Saturday, November 21, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ጉባኤ (COP 31) ላይ የነበራት ተሳትፎ እና የቀጣይ ዓመት ዝግጅት

November 21, 2026
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ጉባኤ (COP 31) ላይ የነበራት ተሳትፎ እና የቀጣይ ዓመት ዝግጅት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአንታልያ ቱርክዬ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል። በቆይታቸውም ከተለያዩ የዓለም መሪዎች ጋር ስኬታማ የሁለትዮሽ ውይይቶችን አድርገዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት የዚህ ታላቅ ጉባኤ (COP 32) አስተናጋጅ ሀገር እንደመሆኗ ዝግጁነቷን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስታውቀዋል።

​የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ከአንታልያ እንደገለጹት፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቆይታቸውን የጀመሩትም ከቱርክዬው ፕሬዝዳንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶሃን ጋር በመወያየት ነው። በውይይታቸውም ቀደም ሲል የተደረጉ የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ትብብር ስምምነቶችን አፈጻጸም ገምግመዋል። ኢትዮጵያ በቀጣዩ ዓመት የምታስተናግደውን ጉባኤ አስመልክቶ ከቱርክዬ ልምድና ድጋፍ በምታገኝበት ሁኔታ ላይም መምክራቸውን ሀላፊዋ አብራርተዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዋናው ጉባኤ ጎን ለጎን ከተለያዩ መሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። ከኖርዌይ፣ ከፊንላንድ፣ ከባርቤዶስ፣ ቦትስዋና እና ከሶማሊያ መሪዎች ጋር በመምከር የቀድሞ የትብብር አጀንዳዎች ያሉበትን ደረጃ መፈተሻቸውን ቢልለኔ ገልጸዋል።

በዋናው የመሪዎች ጉባኤ መክፈቻ መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንደ ቀጣይ የጉባኤው አስተናጋጅ ሀገር መሪ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ መሆኗን አንስተዋል። በድርቅና በጎርፍ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመቀነስ የሜትሮሎጂ ትንበያ ሥርዓቷን በማዘመንና ህብረተሰቡ በምን መልኩ መዘጋጀት እንዳለበት የሚያመለክቱ ቅድመ ዝግጅት እያደረገች መሆኗን አብራርተዋል።

ባለፉት ስምንት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ማንሳታቸውን ቢልለኔ ገልጸዋል። ይህ ተግባር የአካባቢ ጥበቃን ከማረጋገጥ ባለፈ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ የሆነውን የኢትዮጵያ ቡና ምርት ለመታደግ ይረዳል ነው ያሉት። የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎችን ለማጠናከርም ትልቅ ተስፋ ሰጪ እርምጃ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውን አክለዋል።

በተጨማሪም በጉባኤው የተዘጋጀው ሀገርን ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር (ፓቪሊየን) ላይ ኢትዮጵያን ማስተዋወቂያ አምዶች በስፋት መቅረባቸውን ሀላፊዋ ገልጸዋል። በዚህም የቡና እና የሰው ዘር መገኛ አልፎም ​የአትሌቶች እና የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምድር መሆኗን ከዚህም በተጨማሪ በበርካታ ማሳያ አምዶች ኢትዮጵያውያን በስፋት ሀገራቸውን እያስተዋወቁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

​በተጨማሪም ወጣት ተደራዳሪዎች በጉባኤው ላይ እየተሳተፉ የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን አቋም በብቃት እያንጸባረቁ መሆናቸውን አብራርተዋል።

ቢልለኔ ስዩም በቀጣዩ ዓመት አዲስ አበባ የምታስተናግደውን ታላቅ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በስኬት ለማጠናቀቅ ከሆቴልና ከትራንስፖርት እስከ ቱሪዝምና አገልግሎት ዘርፍ የሁሉም ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል።

አክለውም ከመንግስት ዝግጅት ባሻገር የመዲናዋ ነዋሪዎች እና የግል ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ኢትዮጵያዊ እንግዳ ተቀባይነትን በተግባር በማሳየት የጋራ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

​በ – የአብስራ ተፈራ

Source: NBC ETHIOPIA
Via: @NBCETHIOPIA
Tags: #addisababaCop31EthiopiaFacebookMeta
ShareTweetShare
Previous Post

ታላቁ ሩጫ ከጎዳና ሩጫ የተሻገረ ትርጉም ያለው ወሳኝ ስፖርታዊ ኩነት ነው

Next Post

ዘመናዊ የግብርና አሰራር ለሀገራዊ ምርታማነትና ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት መሰረት እየሆነ መጥቷል፦ ምሁራን

Related Posts

ታላቁ ሩጫ ከጎዳና ሩጫ የተሻገረ ትርጉም ያለው ወሳኝ ስፖርታዊ ኩነት ነው
News

ታላቁ ሩጫ ከጎዳና ሩጫ የተሻገረ ትርጉም ያለው ወሳኝ ስፖርታዊ ኩነት ነው

November 20, 2026
12
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ሺ ጂንፒንግና ቭላድሚር ፑቲን ምን ተወያዩ?
International

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ሺ ጂንፒንግና ቭላድሚር ፑቲን ምን ተወያዩ?

November 19, 2026
31
3ኛው ዙር የኮሪደር ልማት፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
News

3ኛው ዙር የኮሪደር ልማት፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

November 19, 2026
18
አዲስ  እና ግዙፍ የውል ስምምነት እየተዘጋጀ ባለበት ወቅት፣ ዴክላን ራይስ ለምን የአርሰናል እጅግ ወሳኝ ተጫዋች ሆኖ እንደሚቀጥል…….
News

አዲስ እና ግዙፍ የውል ስምምነት እየተዘጋጀ ባለበት ወቅት፣ ዴክላን ራይስ ለምን የአርሰናል እጅግ ወሳኝ ተጫዋች ሆኖ እንደሚቀጥል…….

November 19, 2026
22
“ማንቸስተር ሁሌም ‘ሰማያዊ’ ሆኖ አይቀጥልም ” ፖቼቲኖ
News

“ማንቸስተር ሁሌም ‘ሰማያዊ’ ሆኖ አይቀጥልም ” ፖቼቲኖ

November 18, 2026
19
የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
35
Next Post
ዘመናዊ የግብርና አሰራር ለሀገራዊ ምርታማነትና ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት መሰረት እየሆነ መጥቷል፦ ምሁራን

ዘመናዊ የግብርና አሰራር ለሀገራዊ ምርታማነትና ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት መሰረት እየሆነ መጥቷል፦ ምሁራን

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

ዘመናዊ የግብርና አሰራር ለሀገራዊ ምርታማነትና ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት መሰረት እየሆነ መጥቷል፦ ምሁራን

ዘመናዊ የግብርና አሰራር ለሀገራዊ ምርታማነትና ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት መሰረት እየሆነ መጥቷል፦ ምሁራን

November 21, 2026

November 21, 2026
ታላቁ ሩጫ ከጎዳና ሩጫ የተሻገረ ትርጉም ያለው ወሳኝ ስፖርታዊ ኩነት ነው

ታላቁ ሩጫ ከጎዳና ሩጫ የተሻገረ ትርጉም ያለው ወሳኝ ስፖርታዊ ኩነት ነው

November 20, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

ዘመናዊ የግብርና አሰራር ለሀገራዊ ምርታማነትና ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት መሰረት እየሆነ መጥቷል፦ ምሁራን

ዘመናዊ የግብርና አሰራር ለሀገራዊ ምርታማነትና ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት መሰረት እየሆነ መጥቷል፦ ምሁራን

November 21, 2026

November 21, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?