ታላቁ ሩጫ ከጎዳና ሩጫ ባሻገር ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው ወሳኝ ስፖርታዊ ኩነት መሆኑን የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ሰላማዊ ካሳ ገለጹ።

26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር እሁድ ህዳር 13 2019 ዓ.ም ይካሄዳል። ውድድሩን በማስመልከት ዛሬ ጋዜጫዊ መግለጫ ተሰጥቷል።
የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ መዲናችን አዲስ አበባ ደምቃ ለምትውልበት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ዋዜማ እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ከአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ላይ ሩጫ ሆኖ እንዲቀጥል ከማድረጉም በላይ፣ ውድድሩ በዓለም አቀፍ ደረጃም ትልቁ የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ እንዲሆን ለተጀመረው ጥረት አቅም የሚፈጥር መሆኑን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

ይህ ታላቁ ሩጫ ከጎዳና ሩጫ የተሻገረ ትርጉም ያለው ወሳኝ ስፖርታዊ ኩነት መሆኑንም አንስተዋል።
እያንዳንዱ ተሳታፊ ሩጫውን በመጨረስ ይህን ውድድር ከአፍሪካ አልፎ በዓለም መድረክ ትልቁ የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ እንዲሆን ለሚደረገው ጥረት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል።
በታላቁ ሩጫ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በውድድሩ ታሪክ ከፍተኛው ማለትም 60 ሺህ ተሳታፊዎች ይሮጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ውድድሩ በዓለም አትሌቲክስ እውቅና ያለው የጎዳና ላይ ውድድር ነው።









