Thursday, November 19, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Politics International

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ሺ ጂንፒንግና ቭላድሚር ፑቲን ምን ተወያዩ?

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ሺ ጂንፒንግና ቭላድሚር ፑቲን ምን ተወያዩ?

November 19, 2026
in International, News, Politics
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram



ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ በቻይናው ሺ ጂንፒንግ የረዥም ጊዜ ወዳጅ (ኦልድ ፍሬንድ)  ሲባሉ ፤በዶናልድ ትራምፕ የጓደኛዬ ስም ተሰጥቷቸዋል፡፡ የትራምፕ ከእኔ በላይ ማን አለ፤የፑቲን ታክቲክ እና የሺ ስትራቴጂ ጉባዔ በሚልም ተንታኞች የሶስቱን ሀገራት መሪዎች ውይይት  ገልጸውታል፡፡ የዓለም ግዙፍ ኢኮኖሚ፣ጦር ፣ዲፕሎማሲ፣ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀገራት መሪዎች አንድ መድረክ ላይ በሸን’ጀን ቻይና  መገናኘታቸው ታረካዊ ሆኖ ተመዘግቧል፡፡

 ሺ ጂንፒንግ፣ዶናልድ ትራምፕ እና ቭላድሚር ፑቲን የንግግራቸው ውጤት ምንም ይሁን ፤ሶስቱ በአንድ ጠረጴዛ ላይ መገናኘታቸው ታሪካዊ ክስተት አስብሎታል ፡፡ በተናጠል እንጂ ሶስቱ ግዙፎች አንድ ላይ መክረው ፈጽሞ አያውቁም ፡፡የኤዥያ -ፓስፊክ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ጉባኤ (APEC) ደግሞ ለውይይቱ እድሉን ፈጥሯል ፡፡

የፑቲን፣ሺ እና ትራምፕ መገናኘት የ1945ን የጦርነት ጊዜ “የልታ ኮንፈረንስ ” የሚያስታውስም ነው ፡፡ ምናልባትም እንግሊዝ በቻይና፤ክሪሚያ በሸንጀን  ከመተካታቸው ውጭ የዛሬ 8 አስርት ዓመታት ዓለም የነበረችበትን ነውጥ በንጻሬ የሚያሳይ ነው ፡፡ የልታ ኮንፈረንስ ከፈረንጆቹ የካቲት 4-11 /1945 ድረስ ሲካሄድ የዛኔዋ ሶቭዬት ኅብረት ጆሴፕ ስታሊን፣የአሜሪካው ፍራንክሊን ዲ ሩዝቬልት እና የዩናይትድ ኪንግደሙ ዊንስተን ቸርቺል የናዚ ጀርመንን የመጨረሻ ሽንፈት እቅድ ያወጡበት፤ጦርነቱ ሲጠናቀቅም በአውሮፓ ምን ዓይነት ስርዓት ይኑር የሚለውን በግልጽ ያዩበት አጋጣሚ ነበር ፡፡ታዲያ የየልታው ኮንፈረንስ ሞስኮ በምስራቅ አውሮፓ ጡንቻዋን እንድታበረታ እድል የፈጠረ ነው እንደሚባለው ሁሉ፤ዛሬም የፑቲንን ጡንቻ ሊያዳብርላቸው እንደሚችል ተንታኞች ያስቀመጣሉ፡፡

በዘመናዊቷ ዓለም ታሪክ  የሶስቱ ኃይላት፤ የቤይጂንግ ፣ዋሽንግተንና ሞስኮ መሪዎች መገናኘት ዓለም ወደ አዲስ ምዕራፍ እያመራች መሆኑን የሚጠቁምም ያደርገዋል ፡፡ ለዚህም ነው የየልታው ኮንፈረንስ፤ በቻይና ምድር ሸንጀን ታሪክ ተደገመ እየተባለ የሚገኘው ፡፡ የየልታው ኮንፈረንስ በአንድ ግንባር የተሰለፉትን ሞኮስኮን፣ዋሽንግተንና ለንደንን ከ80 ዓመታት በፊት ያገናኘ ሲሆን ዛሬ ላይ በታሪካዊ አጋጣሚ አንድ መድረክ ላይ የተገኙት መሪዎች ግን አጅንዳቸው የየቅል እንደሆነ ይነገራል ፡፡ ሀገራቱ የተለያየ የዓለም አቀፍ ህግ አተገባበር እና ስርዓት ዓላማ ያላቸው ናቸው፡፡
ምናልባትም ሺ ጂንፒንግ እና ፑቲን በተመሳሳይ መድረክ ላይ  ናቸው  ማለት ይቻል ይሆናል እንጂ  ያን ያህል  መሪዎቹ የሀገር ውስጥ ጉዳዮቻቸውን ቸል ብለው ዓይን ለዓይን ተያይተው ይግባባሉ ማለት እንዳልሆነም ታሳቢ ይደረጋል ፡፡  

ውጥንቅጡ በወጣ ዓለም ላይ ሆነው ያደርጉት ውይይት  ውጤቱ እንደትላንቱ በቀላሉ የሚፈታ፤በታሰበው ልክ የሚሄድ እንደማይሆንም  ይገመታል፡፡ ሶስቱም መሪዎች በተለያየ አቋም ላይ ናቸው፡፡ የደብሊን ዩንቨርሲቲ ኮሌጁ የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ፕሮፌሰሩ ስኮት ሉካስ  ጉባዔው የትራምፕ የበላይነት ስሜት፣የፑቲን ታክቲክ እና የሺ ጂንፒንግ ስልታዊነት ነው ማለታቸውም ይህንኑ ያሳያል፡፡ ከባለ 21 ሀገራት ዓባላቱ ኤፔክ ጉባዔ ጎን ለጎን የሦስቱ ግዙፎች ውይይት፤ ብዙ ጥያቄዎችን የሚያነሳ እንጂ መፍትሄ ሰጭ ሊሆን እንደማይችል ቀድሞውንም የተገመተ ነበር ፡፡

ትራምፕ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች ከተገዳዳሪዎች ጋር አለማውራታቸውን ተችተዋል ፡፡ በእርግጥም ዋሽንግተን ከሞሰኮና ቤይጂንግ ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ፍጥጫ አንድም በንግዱ፤አንድም በቴክኖሎጂውና በስለላው፤አለፍ ሲልም በጦር መገዳደሩን በዲፕሎማሲው ካልተካችው መውደቂያዋን እንደማፋጠን ይቆጥሩታል ፡፡

ሪፐብሊካኑ በአትላንቲኩ እና አርክቲኩ እስከ ጥቁር ባህር ጫፍ ሩሲያን ፤በኤዥያ ፓስፊክ እና በኢንዶ ፓስፊኩ ቀጠና ቻይናን ለመገዳደርም ሆነ በአጋርነት አብሮ ለመዝለቅ ዲፕሎማሲን እንምረጥ ሳይሉ አልቀሩም ፡፡ ያም ሆኖ ትራምፕ በተገኙበት መድረክ ሁሉ አሜሪካ አንደኛ ፤በአንጻሩ ሩሲያንና ቻይናን በሁሉም ጉዳይ ከዋሽንግተን ዝቅ አድርገው ደረጃ ይሰጧቸዋል ፡፡  

ትራምፕ የምድሪቱን 52 በመቶ ክፍል የሚካልለውን የኢንዶ -ፓስፊክ ዕዛቸውን ተጠቀመው ቻይናን ከበባ ውስጥ ማስገባት ውጥናቸው ብቻ አይደለም ፡፡ የጂኦፖለቲካ፣ ጂዖቴክኖሎጂ እና የጂኦፋይናንስ ወይም ኢኮኖሚ ተገዳዳሪነትንም የሙጥኝ ብለውታል፡፡ ፕሬዚዳንቱ የዓለምን የፖለቲካ አተነፋፈስ እያዩ የሚቆሙ ሳይሆኑ፤የአሜሪካን የውስጥ ፖለቲካ ግራ ቀኝ እያዳመጡ መጓዝንም መምረጥ ግዴታቸው ሆኗል፡፡

ቻይና እና ሩሲያ በአሁኑ ሰዓት ከወዳጅ በላይ የሚተያዩ ፤ገደብ የለሽ አጋርነት ውስጥ ያሉ ናቸው ፡፡ ሞስኮ በኪዬቭ ላይ ጦር ከቀሰቀሰችበት ጊዜ አንስቶ የሩሲያ ቁጥር አንድ የንግድ ወዳጅ ቻይና ናት ፡፡ ሺ እና ፑቲን ቀድመው ዶልተው ትራምፕን ጠብቀዋቸዋል ፡፡ ፑቲን ከሶስትዮሽ ውይይቱ በፊት የቀድሞ የበላይ ነን ባዮች በሚል ምዕራቡን ዓለም በጥቅሉ፤አውሮፓውያኑን ደግሞ እየደከሙ ያሉ ሲሉ መጥራታቸው ስትራቴጂያቸው ምን ላይ እንዳለ ጠቋሚ ያደርገዋል ፡፡

መሪዎቹ በዝግ ለ1፡30 ያህል ተወያይተዋል ፡፡ የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ደግሞ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ክልከላ እንዲደረግ እና እንዲወድም ጥያቄ አቅርበዋል ፡፡ የኑክሌር ጦርነት በፍጹም አሸናፊ አይኖረውም ፤ሊኖርም አይገባም ፤ከኑክሌር ነጻ ዓለምን እንገንባ የሚል ጥሪም ቀርቧል ፡፡ ሺ ጂንፒንግ ስብሰባውን አዲስ ምዕራፍ የከፈተ እና ታሪካዊ ያሉት ሲሆን ለአዳዲስ ጉዳዮች በር ከፋችም ነው ብለውታል ፡፡ ሶስቱም ሀገራት የቀዝቃዛውን ዓለም ጦርነት ግንዛቤ እርግፍ አድርገው እንዲተውትም ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

ከመገፋፋት አንድ ላይ በኃላፊነት መስራት ወሳኝነት እንዳለውም ፕሬዚዳንቱ አጽንዖት ሰጥተዋል ፡፡ በመከባበር ዓለምን መታደግ ይቻላል ባይ ናቸው ሺ ጂንፒንግ፡፡
ፕሬዚዳንት  ትራምፕ ታሪክ ሰርተናል ሲሉ ቭላድሚር ፑቲንም ሩሲያ፣ቻይናና አሜሪካ ዓለም አቀፍ ደኅንነትን ለማምጣት የጋራ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት የውይይቱ ትኩረት አለመሆኑም ይፋ ሆኗል ፡፡

 “ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ጋር ለመነጋገር ወጥነው ነበር ሳይሳካላቸው ከቻይና ወጡ፤ቻይና ሩሲያ እና አሜሪካ በሶስቱ ሀገራት መካከል ያለው የኃይል ፍሰትን ለማረጋገት ቃል ገቡ፤ሀገራቱ በኑክሌር ጉዳይ ላይ መፍትሄ እንደሚያሻ ተወያዩ፤ባለድሉ ፑቲን ናቸው፤ከሶስትዮሽ ውይይቱ አትራፊው ናቸው”የኢራን ጉዳይ እና መሰል ዓለም አቀፋዊ ክስተቶች የትራምፕ ሺ እና ፑቲን የ1፡30 ቆይታ ጥቅል ሀሳቦች ናቸው፡፡

በ-ቢኒያም ካሴ

Source: @NBCETHIOPIA ​
Tags: chinaPutinRussiatrumpUSA
ShareTweetShare
Previous Post

ለንጉስ ግጥም ከመፃፍ ንጉስ እስከ ማውረድ – ዶክተር ነገደ ጎበዜ

Related Posts

ለንጉስ ግጥም ከመፃፍ ንጉስ እስከ ማውረድ – ዶክተር ነገደ ጎበዜ
Documentary

ለንጉስ ግጥም ከመፃፍ ንጉስ እስከ ማውረድ – ዶክተር ነገደ ጎበዜ

November 19, 2026
5
3ኛው ዙር የኮሪደር ልማት፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
News

3ኛው ዙር የኮሪደር ልማት፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

November 19, 2026
10
አዲስ  እና ግዙፍ የውል ስምምነት እየተዘጋጀ ባለበት ወቅት፣ ዴክላን ራይስ ለምን የአርሰናል እጅግ ወሳኝ ተጫዋች ሆኖ እንደሚቀጥል…….
News

አዲስ እና ግዙፍ የውል ስምምነት እየተዘጋጀ ባለበት ወቅት፣ ዴክላን ራይስ ለምን የአርሰናል እጅግ ወሳኝ ተጫዋች ሆኖ እንደሚቀጥል…….

November 19, 2026
18
ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ
Hard Talk

ፋኖ ፀረ-ሰላም ኃይል ነው-የቀድሞው የፋኖ አመራር ማርእሸት ፀሐዩ

November 18, 2026
72
“ማንቸስተር ሁሌም ‘ሰማያዊ’ ሆኖ አይቀጥልም ” ፖቼቲኖ
News

“ማንቸስተር ሁሌም ‘ሰማያዊ’ ሆኖ አይቀጥልም ” ፖቼቲኖ

November 18, 2026
17
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ
#ethiopia

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
14

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ሺ ጂንፒንግና ቭላድሚር ፑቲን ምን ተወያዩ?

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ሺ ጂንፒንግና ቭላድሚር ፑቲን ምን ተወያዩ?

November 19, 2026
ለንጉስ ግጥም ከመፃፍ ንጉስ እስከ ማውረድ – ዶክተር ነገደ ጎበዜ

ለንጉስ ግጥም ከመፃፍ ንጉስ እስከ ማውረድ – ዶክተር ነገደ ጎበዜ

November 19, 2026
3ኛው ዙር የኮሪደር ልማት፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

3ኛው ዙር የኮሪደር ልማት፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

November 19, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ሺ ጂንፒንግና ቭላድሚር ፑቲን ምን ተወያዩ?

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ሺ ጂንፒንግና ቭላድሚር ፑቲን ምን ተወያዩ?

November 19, 2026
ለንጉስ ግጥም ከመፃፍ ንጉስ እስከ ማውረድ – ዶክተር ነገደ ጎበዜ

ለንጉስ ግጥም ከመፃፍ ንጉስ እስከ ማውረድ – ዶክተር ነገደ ጎበዜ

November 19, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?