።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ፣ ማንቸስተር ዩናይትድን በከተማዋ እጅግ ስኬታማ የእግር ኳስ ክለብነት ወደነበረበት ቦታ እንደሚመልሰው ተናግሯል።
አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ፣ ለሁለት ዓመት ተኩል የሚቆይ ውል ከተፈራረሙ በኋላ፣ ረቡዕ ዕለት አዲሱን የማንቸስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝነት ኃላፊነት ይረከባሉ።
ማክሰኞ ዕለት በሲንሲናቲ በተደረገውና እርሳቸው በኃላፊነት የመሩት የመጨረሻ ጨዋታ፣ አሜሪካ ሄይቲን 2 ለ 0 አሸንፋለች፤ ከጨዋታው በኋላም ፖቼቲኖ ለ’ቲኤንቲ ስፖርትስ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
እ.ኤ.አ. በ2006-07 የውድድር ዘመን በማንቸስተር ሲቲ በውሰት ተጫዋችነት ያሳለፈው ደማርከስ ቢስሊ፣ “ማንቸስተር ሰማያዊ ነው፤ ሁሌም ሰማያዊ ሆኖ ይኖራል” ሲል በቀልድ መልክ ተናግሯል።
ፖቼቲኖም ሲመልስ፣ “በፍጹም፤ ገና ታያላችሁ። ጊዜ ስጡኝና ነገሮች ይለወጣሉ” ብሏል።
ቀደም ሲል ቼልሲን፣ ቶተንሃምን እና ሳውዝሃምፕተንን ያሰለጠኑት ፖቼቲኖ፣ ከጨዋታው በኋላ በቀጥታ በግል አውሮፕላን ወደ ማንቸስተር እንዳቀኑ ተነግሯል።
“አዲሱ ፈተና ትልቅ በመሆኑ በጣም ጓጉተናል፤ ይህ ደግሞ አንድ ሰው ሊሰማው የሚፈልገው ዓይነት ጉጉት ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
“የምንሠራው ሥራ የተለየ ይሆናል፤ ነገር ግን ይህንን ለመወጣት የሚያስችል ልምድ አለን። ነገሮችን በምንቀርብበት መንገድ ላይ አስተዋይነትን (common sense) ማከል ይኖርብናል።”
“ማንቸስተር ዩናይትድ እንደ ክለብም ሆነ ደጋፊዎቹ፣ አሁን ካሉበት ሁኔታ የተሻለ ደረጃ ሊኖራቸው እንደሚገባ እናውቃለን።”
ማክሰኞ ዕለት የተገኘው ድል፣ አሜሪካ ወደ ‘ኮንካካፍ ኔሽንስ ሊግ’ ግማሽ ፍጻሜ እንድታልፍ አድርጓታል፤ እንዲሁም ፖቼቲኖ በኃላፊነት በቆዩባቸው 37 ጨዋታዎች 62.16% የማሸነፍ ንጻሬን አስመዝግበዋል።
ዕድሜያቸው 54 ዓመት የሆነው አሰልጣኙ፣ ቡድኑን እስከ 2025 ‘ጎልድ ካፕ’ ፍጻሜ እንዲሁም አሜሪካ በጋራ አስተናጋጅነት ወደተሳተፈችበት የ2026 የዓለም ዋንጫ እስከ 16ቱ ዙር አድርሰዋል።
በኢንስታግራም ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መግለጫ፣ “ስለ አሳካነው ነገር ኩራት ይሰማኛል” ብለዋል።
“ቡድኑን ስረከብ፣ ከማንኛውም ተጋጣሚ ጋር መወዳደር እንደምንችል እንድናምን ፈልጌ ነበር። ዛሬ ላይ ይህ እምነት በተጫዋቾቹ ብቻ ሳይሆን፣ ቡድኑን በሚደግፉ ሰዎች ሁሉ ዘንድ የበለጠ ጠንክሮ እንደሚገኝ ተስፋ አደርጋለሁ።” “ይህ ተሞክሮ አዲስ ጉልበት ሰጥቶኛል፤ በእግር ኳስም ሆነ በግል ህይወቴ ብዙ ነገር አበርክቶልኛል።
“በዚህ ወቅት መሄድ ከባድ ቢሆንም፣ በእግር ኳስ ውስጥ አንዳንዴ ‘አይሆንም’ ለማለት የማይቻልበት አጋጣሚ ይፈጠራል። በጣም ደስተኛ በነበርኩበት ቦታ መተው ቢያስፈልግም እንኳ፣ ሁልጊዜም ልቤ የሚነግረኝን መከተል እንዳለብኝ አምናለሁ።
“ይህ ቡድን ማደጉን እንደሚቀጥል እና የሚገባውን ስኬት ሁሉ እንደሚያሳካ ተስፋ አደርጋለሁ።”
በ-ሳምሶን አበበ
። ። ።
ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) በመጫን NBC ኢትዮጵያን ይጎብኙ ይወዳጁ
https://linktr.ee/NBCEthiopiaTV
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘት
#Ethiopia









