የኖቲንግሃም ፎረስቱ ተጫዋች አሌክሳንደር ዚንቼንኮ በምሽቱ ጨዋታ በጉዳት ሳቢያ እንደማይሰለፍ ተገለጸ።
የውድድር አመቱ በውሰት ውል ለማሳለፍ ከአርሰናል ወደ ሲቲ ግራውንድ ያቀናው ዩክሬናዊ የግራ መስመር ተከላካይ ባጋጠመው የብሽሽት ጉዳት ከሚቺላንድ ከሚደረገው የምሽቱ ጨዋታ ውጪ ተደርጓል።
ዚንቼንኮ ጉዳቱ የገጠመው ባሳለፍነው ቅዳሜ ፎረስት ከሰንደርላንድ ባደረጉት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ እንደነበር ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ከምሽቱ ጨዋታ አስቀድሞ ጋዜጣሚ መግለጫ የሰጡት አሰልጣኝ አንጅ ፖስትኮግሉ፣ ዚንቼንኮ በሰንደርላንዱ ጨዋታ መጠነኛ ጉዳት የገጠመው ቢሆንም፤ አሁን ላይ ለመጫወት የሚሰጠው ባለመሆኑ አይሰለፍም ብለዋል።
አሰልጣኙ አያይዘውም ተጫዋቹ በአርሰናል ቤት ባለፉት የውድድር አመታት ካደረገው መጠነኛ ጨዋታ አኳያ እኛጋ በርካታ ጨዋታዎችን እያደረገ መሆኑ ለጉዳት አጋልጦታል ያሉ ሲሆን፤ የፊታችን እሁድ ከኒውካስትል ዩናይትድ ጋር በሚደረገውም ጨዋታ እንደማይደርስ ገልጸዋል።
ፎረስት በምሽቱ ጨዋታ ከዚንቼንኮ በተጨማሪ የዳግላስ ልዊዝ እና ኦላ አይናን ግልጋሎትም በጉዳት ሳቢያ የማያገኝ ይሆናል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












