
አንድ አሜሪካዊ የጂምናስቲክ አትሌት ከአራት ወራት በላይ ጠንካራ ስልጠና በኋላ፥ ጣቶቹን አጥፎ በእጆቹ በመቆም (knuckle handstand) 1 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በመቆየት ሪከርድ ሰብሯል።
የ20 ዓመቱ ማደን ሼሊ ከ6 ዓመቱ ጀምሮ ጂምናስቲክ ሲሰራ የነበረ ሲሆን፣ አንድ ቀን በኦሎምፒክ ለመወዳደር ያልም እንደነበር ገልጿል። ነገር ግን የአከርካሪ አጥንት መንሸራተት እና የአጥንት ስንጥቆች ከስልጠና እንዲርቅ አስገድደውታል።
ከጉዳቶቹ በማገገም ላይ በነበረበት ወቅት የጊነስ የዓለም ሪከርዶች የስፖርት እና የአካል ብቃት ክብረ ወሰኖችን ሲያነብ፣ ጣቶቹን አጥፎ መሬት ላይ በመደገፍ እና ሙሉ በሙሉ በእጆቹ በመቆም ረገድ ለወንዶች ለረጅም ጊዜ የመቆይታ ሪከርድን ለመያዝ ወሰነ።
ማደን እንደተናገረው፥ ወርባጣቶች ላይ ተገልብጦ መቆም ፍጹም ያልተለመደ የጂምናስቲክ እንቅስቃሴ በመሆኑ፥ ስለዚህ የተለያዩ ዘዴዎችን በመሞከር እና ሌሎች አትሌቶች እነዚህን ክህሎቶች እንዴት እንደሚፈጽሙ የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን በመመልከት መሰረታዊ ቴክኒኩን ለማወቅ አንድ አሳልፏል።
ሁለተኛው የስልጠና ምዕራፍ በታጠፉ ጣቶቹ ላይ ሚዛኑን ጠብቆ የመቆም ልምምድ ሲሆን ይህም ስድስት ሳምንታት እንደፈጀበት ተናግሯል።

“በሶስተኛው የስልጠና ምዕራፍ፣ ከስድስት ሳምንታት በላይ፣ የሰውነቴን ክብደት በጣቶቼ ጀርባ ላይ አሳርፌ ላይ ከአንድ ደቂቃ በላይ በመሸከም የሚመጣውን ህመም ለመቋቋም የሚያስችል ጽናት አዳብሬአለሁ፤ ይህ ህመም ከፍተኛ ነበር” ብሏል።
“ከእያንዳንዱ ሙከራ በኋላ፣ የጣት መገጣጠሚያዎቼ ያብጡ ነበር፤ ስለዚህ በልምምዴ መሃል እረፍት አድደርጋለሁ፣ እንዲሁም ከስልጠና ክፍለ ጊዜዎች በኋላ ጣቶቼ ላይ በረዶ እያደረግኩ ቆይቻለሁ።”
ከዚህ የወራት ልምምድ በኋላ ይፋዊ ሙከራውን ያደረገ ሲሆን፥ ለ1 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በመያዝ ሪከርዱን ለመውሰድ ችሏል። ሪከርዱም በጊነስ የዓለም ሪከርዶች ጸድቋል።












