ፖርቱጋላዊው ተከላካይ በውሃ ሰማያዊዎቹ ቤት እስከ አውሮፓውያኑ 2029 የሚያቆየውን የ4 አመት ኮንትራት መፈረሙን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
በ2020 ከቤኔፊካ ማንችስተር ሲቲን የተቀላቀለው ዲያዝ በክለቡ ያለፉት አመታት ስኬት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካላቸው ተጫዋቾች አንዱ መሆኑን አሳይቷል።
ማንችስተር ሲቲ በጥር የዝውውር መስኮት በመሃል ተከላካይ ስፍራ ላይ አብዱኮድር ኮዣኖቭ እና ቪክቶር ሬይስን ማስፈርሙን ተከትሎ፤ ዲያዝ ሊለቅ ይችላል ቢባልም በኤቲሃድ መቆየትን ፈልጓል።
የ28 አመቱ ሩበን ዲያዝ ለኤርሊንግ ሃላንድ ከተሰጠው የ9 አመት ኮንትራት በመቀጠል የረጅም አመት ውል የተሰጠው ተጫዋች ሆኗል። ተጫዋቹ በመጀመሪያው ሳምንት ሲቲ ወልቭስን በገጠመበት ጨዋታ ከጆን ስቶንስ ጋር ተጣምሮ መጫወቱ አይዘነጋም።
በያዝነው አመት ወደ ቀደመ ከፍታው ለመመለስ በሚያልመው የጋርዲዮላ ቡድን ውስጥ ቁልፍ ሚና ይሰጠዋል ተብሎም ይጠበቃል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












