“እንኳን ለሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል እና እንግጫ ነቀላ በዓላት አደረሳችሁ።
ባሕል የአንድ ማህበረሰብ ቁሳዊና መንፈሳዊ ትውፊት የሚያንፀባርቅበት የታሪክ አሻራ ነው፡፡ ሐብትና የማንነት መግለጫም ነው። በየዓመቱ በክልላችን በተለያዩ አካባቢዎች የሚከበሩት ባሕላዊና ኃይማኖታዊ በዓላት የማሕበራዊ ግንኙነት ማሳለጫ እሴቶች ናቸው።
በአዲስ ዓመት መሸጋገሪያ ወቅት በድምቀት የሚከበሩት የሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል፣ እንግጫ ነቀላ እና ከሴ አጨዳ በዓል ልጃገረዶች ዘንድ በልዩ ልዩ ኩነቶች ደምቀው ይከበራሉ።
ልጃገረዶቹ አዲሱን ዘመን በደስታና በሀሴት ለመቀበል በአብሮነት በብሩህ ተስፋ ውስጥ ሆነው በጋራ የሚያከብሩት በዓል ነው። የነጻነትና የአብሮነታቸው ማድመቂያ፤ የመተሳሰብና የፍቅር ማብሰሪያቸው ነው።
በዓሉ የሕዝባችን አንድነትና የርስበርስ ትስስርን ለማጠናከር ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ባሕላዊና ኃይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ ለትውልድ ማቆየት ያስፈልጋል። የሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል፣እንግጫ ነቀላ እና ከሴ አጨዳ በዓል ከሕዝባችን መገለጫነት አልፎ በአለም ቅርስነት እንዲመዘገብ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን።
መልካም በዓል “












