እንደ ዘ አትሌቲክ ዘገባ አሁን ላይ የተደረሰ ምንም አይነት ስምምነት ባይኖርም ድርድሮች ግን በአዎንታዊ መንገድ እየሄዱ ይገኛሉ።
የ22 አመቱን ተጫዋች ለማስፈረም ከኖቲንግሃም ፎረስት በዘለለም ኤይንትራክት ፍራክፈርቶች ካሰለፍነው ክረምት ጀምሮ ሲከታተሉት ቆይተዋል። ፎረስቶች ዳኒሎ እና ልዊስ ኦብርየንን በያዝነው የዝውውር መስኮት መሸጣቸውን ተከትሎ ተጫዋቹን እንደ ስምንት አልያም አስር ቁጥር ለመጠቀም ፍላጎቶችን ማሳየታቸው ተገልጿአል።
ተጫዋቹ ከክለብ አለም ዋንጫ ይልቅ የ21 አመት በታች የአውሮፓ ዋንጫ ላይ መሳተፍን መርጦ ሀገሩ እንግሊዝን በአምበልነት እየመራ የተሳካ ጊዜ ማሳለፍ ችሏል። በተጠናቀቀው የውድድር አመት ለሲትዝኖቹ 27 ጨዋታዎች ላይ የተሳተፈ ሲሆን በፕሪምየር ሊጉ የጀመራቸው ጨዋታዎች ቁጥር ግን 3 ብቻ ናቸው።
በማንቸስተር ሲቲ ቤት እስከ 2026 የሚቆይ ኮንትራት ያለው ማካቲ በሊጉ በሼፊልድ ዩናይትድ ቤት ባሳለፈው የውሰት ቆይታው 2023-24 ላይ 30 ጨዋታዎችን ማድረጉም የሚታወስ ነው።












