ኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዙሪያ በቀረጿቸው አጀንዳዎች ላይ ትክክለኛ መረጃን በማድረስ ላበረከተው አስተዋጽኦ እውቅና አገኘ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራ አስኪያጅ ጽ/ቤት፣ ለ ናሽናል ሚዲያ (ኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ) የዕውቅና እና የምስጋና የምስክር ወረቀት አበርክቷል። የእውቅና ይምስክር ወረቀቱን የተቀበሉት የናሽናል ሚዲያ አ.ማ (ኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ) ም/ ዋና ስራ አስፈጻሚ ታደሰ ዳኛቸው ናቸው፡፡

ምስክር ወረቀቱ የተሰጠው ሚዲያው በ2017 ዓ.ም በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዙሪያ በቀረጿቸው አጀንዳዎች ላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች ትክክለኛ መረጃን በማሰራጨት ግንዛቤ እንዲያገኙ ላደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነው።
ከናሽናል ሚዲያ (ኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ) በተጨማሪ ለሌሎች አራት የመንግስት እና ሁለት የግል መገናኛ ብዙሀን ተቋማት የእውቅና የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል። የአዲስ አበባ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ዕውቅናውን የሰጠው በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ ነው።












