ትውልደ ኤርትራዊውን አጥቂ አሌክሳንደር ኢሳቅን የማጣት አደጋ ውስጥ የገባው ኒውካስትል ከተለያዩ የፊት መስመር ተጫዋቾች ጋር ስሙ ተያይዞ እየተነሳ ይገኛል።
ኒውካስትል የኖቲንግሃም ፎረስቱን አጥቂ ዮሃን ዊሳን ለማስፈረም ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ከሆነበት በኋላ ፊቱን ወደ አርቢ ላይብዚሹ አጥቂ ቤንጃሚን ሼሽኮ አዙሯል። ቤንጃሚን ሼሽኮ በዝውውር መስኮቱ ወደ አርሰናል ይጓዛል በሚል ሲዘገብ ቢቆይም፣መድፈኞቹ ፍላጎታቸው ቪክቶር ዮኬሬሽን ማስፈረም ሆኗል።
የአሰልጣኝ ኤዲ ሆው ቡድን ኒውካስትል ተጫዋቹን ወደ ሴንት ጄምስ ፓርክ ለማምጣት ሂደቱን የጀመረ ሲሆን፣ለዝውውሩ እስከ 80 ሚሊዮን የመክፈል ፍላጎት አለው ተብሏል። ማግፓይሶቹ በቀጣይ የውድድር አመት ቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ መሆናቸው ተጫዋቹን ለማግኘት እንደሚረዳቸው ይታመናል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












