አስቶን ቪላ የተስፈኛውን የአማካኝ ስፍራ ተጫዋች ውል እስከ አውሮፓውያኑ 2030 ማደሱን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
የ25 አመቱ ፈረንሳዊ ክለቡ ከአውሮፓ ውድድር ተሳትፎ መውጣቱን ተከትሎ ሊለቅ ይችላል ቢባልም፣ በቪላ ፓርክ ለተጨማሪ 5 አመት የሚያቆየውን ውል ፈርሟል። ተጫዋቹ በክለቡ የነበረውን ውል ሊጠናቀቅ 2 አመት ብቻ ይቀረው የነበረ ሲሆን፤ በበርካታ የጣሊያን ክለቦች በዝውውር ገበያው ተፈላጊ ሆኖ ነበር።
ቡባካር ካማራ በተጠናቀቀው የውድድር አመት በACL ጉዳት ከሜዳ እስኪርቅ ድረስ የአሰልጣኝ ኡናይ ኢምሬ የመጀመሪያ አሰላለፍ ላይ ከሚካተቱ ወሳኝ ተጫዋቾች አንዱ እንደነበር ይታወሳል።
ተጫዋቹ የበርኒንግሃሙን ክለብ የተቀላቀለው በ2022 ከፈረንሳዩ ኦሎምፒክ ማርሴይ መሆኑም ይታወሳል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












