የቶተንሃም ሆትስፐሩ ታሪካዊ ተጫዋች ከ10 አመታት ቆይታ በኋላ ከሰሜን ለንደኑ ክለብ ሊለቅ መቃረቡን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ደቡብ ኮሪያዊው የክንፍ ተጫዋች ከሳዑዲ አረቢያ ክለቦች ጥያቄ ቢቀርብለትም ፍላጎቱ ወደ አሜሪካው ሜጀር ሊግ ሶከር መጓዝ ነው ተብሏል። በሜጀር ሊግ ተሳታፊ የሆነው ሎስ አንጀለስ የሰን ፈላጊ ሲሆን፤ ለቶተንሃም ሆትስፐር ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ ማቅረቡ ተሰምቷል።
ቶተንሃም ለተጫዋቹ ዝውውር ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ፓውንድ ከቀረበለት ፈቃደኛ እንደሚሆን ታውቋል። የ33 አመቱ ሰን በአሁኑ ጊዜ ለቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት በእስያ በሚገኘው የአሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ የቡድን ስብስብ ውስጥ ይገኛል።
በመጪዎቹ ቀናትም ዝውውሩን በሚመለከት ከክለቡ እንደሚነጋገር ተዘግቧል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












