የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን አስመልክቶ የ2017 በጀት አመት የስራ አፈፃፀምና የ2018 ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ፅ/ቤት መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ኃላፊ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ ከሰሞኑ በከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የጎርፍ አደጋ መከሰቱን ገልፀዋል።
ለነዚህ የጎርፍ አደጋዎች መከሰት የጣለው ዝናብ ከበድ ያለ መሆኑን ተከትሎ እንደሆነ ጠቁመው በአደጋዎቹም በሰው ህይወት ላይ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰ ተናግረዋል። በንብረት ላይ የደረሰ ከባድ ውድመት አለመኖሩን ገልፀው አጠቃላይ አደጋው ያደረሰው የጉዳት መጠን በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።
የጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ 348 ቦታዎችን በመለየት የማቅለል ስራ መሰራቱን የገለፁት ኃላፊው ከ7 መቶ በላይ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎችን ችግሩ በዘላቂነት እስኪፈታ ድረስ ከስፍራው ማራቅ መቻሉን አስረድተዋል።
በ – አክረም ኑርያ












