የኦሮሚያ ክልል በ2018 በጀት ዓመት በክልሉ በሚከናወኑ ኢንቨስትመንቶች ለአንድ ሚሊዮን ዜጉች የስራ እድል ለመፍጠር ማቀዱ ተገለጸ::
የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ የክልሉን የ2018 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድን በተመለከተ ለጋዘጤኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል በ2018 በጀት ዓመት 10 ሺህ 500 የኢንቨስትመንት ፕሮጄክቶችን ተግባራዊ በማድረግ 200 ቢሊዮን ብር ካፒታል ለማስመዝገብ መታቀዱን ኃለፊው ገልጸዋል፡፡
በበጀት ዓመቱም በሚከናወኑ ኢንቨስትመንቶች ለአንድ ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር መታቀዱ ነው የተጠቆመው፡፡ እንዲሁም በክልሉ ሰላምን ለማረገገጥ ፤በትጥቅ ትግል ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን ወደ ሰላም ለማምጣት የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚሰሩ ተገልጿል::
ክልሉ በልማት ስራዎቹ ከሚያከናውናቸው ስራዎች የ2017/2018 የበልግ ግብርና 41 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅም ተመላክቷል፡፡
የኦሮሚያ ክልል በ2018 በጀት ዓመት የኢንቨስትመንት ፕሮጄክቶችን ለማስፋፋት እንደሚሰራ የጠቆሙት የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ የንጹህ ዉሃ መጠጥ ፕሮጀክት ግንባታ ለማሳደግም እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
በ ሰላም ይልማ












