የኢንትራክት ፍራንክፈርቱ አጥቂ ሊቨርፑልን ለመቀላቀል የህክምና ሂደት ለማጠናቀቅ መርሲሳይ መድረሱ ተዘግቧል።
ሻምፒዮኑ ሊቨርፑል በዝውውር ገበያው በንቃት እየተሳተፈ ሲሆን፤ የ22 አመቱ ተጫዋች 4ኛው አዲስ ፈራሚ ተጫዋች ሆኖ ይተዋወቃል።
ሊቨርፑል በተመሳሳይ ከጀርመኑ ክለብ ባየር ሊቨርኩሰን አማካኙን ፍሎሪያን ቪትዝን 130 ሚሊዮን ፓውንድ በመክፈል ሪከርድ ሂሳብ ወጪ ያደረገ ሲሆን፤ ለኤኪቲኬም ከፍተኛ የተባለውን 95 ሚሊዮን ፓውንድ ከፍሏል።
የአሰልጣኝ አርነ ስሎት ቡድን በተከታታይ አመት ሻምፒዮን ለመሆን የሚያስችለውን የቡድን ስብስብ በማዘጋጀት ላይ ይገኛል። በቀኝ መስመር ተከላካይነት ጄረሚ ፍሪምፖንግን፣ በግራ ማስመር ሚሎስ ኬርኬዝን በአማካኝ መስመር ፍሎሪያን ቪትዝን እና አሁን ደግሞ በአጥቂ ስፍራ ሁጎ ኤኪቲኬን የራሱ አድርጓል።
ሁጎ ኤኪቲኬ በቀጣይ 24 ሰዓታት ውስጥ በአንፊልድ እስከ 2031 የሚያቆየውን የስድስት አመት ውል ይፈርማል ተብሎ ይጠበቃል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












