በዝውውር መስኮቱ እጅግ አሰልቺ የሆነው የስዊድናዊው አጥቂ የሰሜን ለንደን ዝውውር በስተመጨረሻ መጠናቀቁን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ሁለቱን ክለቦች ለሳምንታት ሳያግባባ የቆየው እና ዝውውሩን ያጓተተው የተጫዋቹ ስኬቶች ላይ የተመሰረቱ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎችን በተመለከተ የፖርቱጋሉ ክለብ የሚያነሳቸው ነጥቦች በአርሰናል ተቀባይነት ማጣታቸው ነበር ተብሏል።
አርሰናል ለዝውውሩ የመነሻ 63.5 ሚሊዮን ፓውንድ ውጪ የሚያደርግ ሲሆን፣10 ሚሊዮን ፓውንድ ተጨማሪ ክፍያ በተጫዋቹ አቋም ላይ ተመስርቶ የሚከፍል ይሆናል። ማንችስተር ዩናይትድ ዝውውሩን ለመጥለፍ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም፣የተጫዋቹ ፍላጎት መድፈኞቹን መቀላቀል ሆኗል።
የ27 አመቱ ቪክቶር ዮኬሬሽ በቀጣይ 48 ሰዓታት የህክምና ሂደቱን በማጠናቀቅ ወደ ሲንጋፖር ያቀናውን የአልጣኝ ሚኬል አርቴታን የቡድን ስብስብ ይቀላቀላል። ዮኬሬሽ በተጠናቀቀው የውድድር አመት በ52 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 52 ግቦችን በስሙ አስመዝግቧል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












