ታሪካዊው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እና የዌልስ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች በህመም ሳቢያ በ70 አመቱ ህይወቱ አልፏል።
ዌልሳዊው የቀድሞ የግራ መስመር ተከላካይ በሊቨርፑል ቤት ከአውሮፓውያኑ ከ1975 እስከ 1978 ከዚያም ወደ ቼልሲ በመጓዝ እስከ 1982 ተጫውቷል። በሰማያዊዎቹ ቤት 2 አመት ከተጫወተ በኋላ ወደ ልጅነት ክለቡ ሬክስሃም በሄድ ጥቂት አመታት ቆይቶ ጫማውን ሰቅሏል።
ጆንስ በሊቨርፑል በነበረው የሶስት አመት ቆይታ 100 ጨዋታዎች ላይ መሰለፍ የቻለ ሲሆን፤ ከቀዮቹ ጋር 2 የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ እና በአሁኑ መጠሪያው ይሮፓ ሊግ የተባለውን ዋንጫ ማሳካት ችሏል።
ለሃገሩ ዌልስም 72 ጨዋታ በማድረግ ቀዳሚው ብዙ ጨዋታ ያደረገ ተጫዋች በመባል በጋሬዝ ቤል ሪከርዱ እስኪሻሻል ስሙን አስመዝግቧል። የጆይ ጆንስ የቀድሞ የቡድን አጋሮቹ እና ሲጨወት የተመለከቱ ደጋፊዎች ሃዘናቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












