የቀድሞው የአርሰናል፣ባርሴሎና እና ቼልሲ አጥቂ ከሳዑዲ አረቢያው ክለብ አል ቃዲሽ ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ በነጻ ሊለቅ መሆኑን ታማኝነት ያለው መረጃ የሚያወጡ መገናኛ ብዙሃን ዘግበውታል።
አል ቃዲሽ ወጣት አዲስ አጥቂ ለማስፈረም በዝግጅት ላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ከኦባምያንግ ወኪሎች ጋር በመነጋገር ላይ መሆኑ ታውቋል። የ36 አመቱ አጥቂ ከአል ቃዲሽ ጋር ኮንትራቱን በስምምነት በማፍረስ በቀጣዮቹ ቀናት ነጻ ተጫዋች ይሆናል ተብሏል።
ጋቦናዊው ኦባምያንግ በተጠናቀቀው የውድድር አመት በ36 ጨዋታዎች ተሰልፎ 21 ግቦችን ሲያስቆጥር፣3 ወደ ግብ የተለወጡ ኳሶችን ማቀበል ችሏል። ተጫዋቹ ምንም እንኳን አስደናቂ የውድድር አመት ቢያሳልፍም፣ክለቡ የተጋነነ ወጪ የሚከፍልበትን ውል በስምምነት እንዲፈርስ መፈለጉ ተገልጿል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












