የሰሜን ለንደኑ ክለብ ጃፓናዊውን ተከላካይ በጃፓን ሊግ ከሚወዳደረው ካዋሳኪ ፍሮንታሌ በ5 ሚሊዮን ፓውንድ የግሉ አድርጎታል።
የ20 አመቱ ኮታ የአምስት አመት ውል የፈረመ ሲሆን የሚኪ ቫንደቭን ወይም ኬቭን ዳንሶ አጣማሪ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ታዳጊው ተጫዋች በሃይል የተሞላና እና በአንድ ለአንድ ግንኙነት በሚያሳየው አስደናቂ ብቃት ተደናቂነትን አግኝቷል። ቶተንሃም ተስፋ የተጣለበትን ተጫዋች ያገኘበት አነስተኛ ገንዘብም አትራፊ ያደርገዋል እየተባለ ይገኛል።
ተጫዋቹ ለክዋሳኪ 81 ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን፣ ቡድኑን ለእስያ ቻምፒዮን ሊግ ፍጻሜ በማድረስ እና በጥሎ ማለፍ ከአልናስር ጋር በተደረገ ጨዋታ ክሪስትያኖ ሮናልዶን የተቆጣጠረበት መንገድ ሙገሳ እንዲቸረው አድርጓል።
በጃፓን ሊግ የአመቱ ኮከብ ተጫዋችነት ሽልማትንም አግኝቷል። ኮታ ታካይ ለቶተንሃም በክረምቱ ሁለተኛው ፈራሚ በመሆን የቶማስ ፍራንክን የቡድን ስብስብ ተቀላቅሏል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












