የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደቡብ ኮሪያ “ለራሷ መከላከያ የግድ መክፈል” እንደሚጠበቅባት አስገነዘቡ፡፡
ደቡብ ኮሪያ የአሜሪካ ጦር ስለሚጠብቃት መደገፍ እና መክፈል ይኖርባታል በሚል አሳስበዋል፡፡ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ “የወጭ ቅነሳ አካሄድ” አሜሪካን በቀጠናው አጋር ሊያሳጣት እንዳይችልም ተሰግቷል፡፡
“ይህ እጅግ ልክ ያልሆነ ነው ፤ ለበርካታ ስኬታማ አገራት ጦር እናቀርባለን” ሲሉ ትራምፕ በዋይት ሀውስ በካቢኒያቸው ስብሰባ ወቅት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ ደቡብ ኮሪያ እጅግ በርካታ ገንዘብ እንደምትሰራ እና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለች ያስታወሱት ሪፐብሊካኑ፣ ለራሷ ጦር መክፈል ይጠበቅባታል በሚል አሳስበዋል።
ይህ ማለት ደቡብ ኮሪያን ለሚጠብቃት የአሜሪካ ጦር ገንዘብ ትክፈል ነው፡፡ ትራምፕ በመጀመሪያው ዙር የፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው ሴዑል ለዋሽንግተን ጦር ለመክፈል መስማማቷን ግልጽ ቢያደርጉም፣ ዴሞክራቱ ባይደን ወደ ዋይት ሀውስ ሲገቡ ሰርዘውባቸዋል።
ደቡብ ኮሪያውያን በዓመት 10 ቢሊዮን ዶላር መክፈል እንዳለባቸው ነግሪያቸው ነበር ብለዋልም ፕሬዚዳንቱ ዶናልድ ትራምፕ፡፡
ሮይተርስ እንዳስነበው።
በ-ቢኒያም ካሴ












