። ። ። ። ። ። ። ። ።
አሜሪካ ኢራን ዩራኒዬም ማበልጸጓን የግድ ማቆም አለባት አለች ፡፡
ቴህራን ዩራኒዬም ማበልጸጓን ማቆም እንዲሁም ማስወገድ ይጠበቅባታል ብለዋል በመካከለኛው ምስራቅ የዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ፡፡
ተወካዩ ኢራን ዩራኒዬም በዝቅተኛ ደረጃ ማብላላት ትችላለች ከሚለው የቀደመ ሀሳባቸው ያፈነገጠ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
ኢራን እንዲህ ዓይነቱ ሀሳብ ላይ የመስማማቷ ነገር አስቸጋሪ በመሆኑ፣ ዊትኮፍ ለሁተኛው ዙር ድርድር ሳንካ ፈጥረዋል ተብሏል፡፡
ከዋሽንግተን ጋር ለመስማማት አማራጩ ይህን ማድረግ ነው ዓይነት አቋምም አራምደዋል።
ሁለተኛው ዙር ድርድር በሮም ሊደረግ ይችላል ቢባልም አፍራሽ ሀሳቦች ከዋሽንግተን በኩል ወጥተዋል፡፡
“የትኛውም የመጨረሻ ስምምነት በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሁም ብልጽግናን ማረጋገጥ አለበት” ባይ ናቸው ዊትኮፍ፡፡
ይህን ለማድረግ ደግሞ ቴህራን ዩራኒዬም ማበልጸጓን መተው አለባት ነው የሚሉት።
በተለይም በኑክሌር ድርድሩ ዙሪያ የሩሲያን ፖለቲከኞች ለማማከር የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰይድ አባስ አራግቺ ወደ ሞስኮ በቀናት ውስጥ ይጓዛሉ መባሉን ተከትሎ ዊትኮፍ የሰጡት መግለጫ መሆኑ ጥያቄ አስነስቷል፡፡
ዘገባው የዋሽንግተን ፖስት ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












