፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ በማዕከል ደረጃ ለ5 ሺህ በየክፍለ ከተሞች ደግሞ 2 መቶ ሺህ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር እያከናወነ ይገኛል።
ከተማ አስተዳደሩ በ2017 ያከናወናቸው የማዕድ ማጋራት ፕሮግራሞች ይህኛው ለ8ኛ ጊዜ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

በዚህ የበጎ ፈቃድ ስራ ላይ በርካታ ባለሀብቶችና ድርጅቶች መሳተፋቸውን ገልፀው ይህም ጊዜያዊ ችግሮችን በመደጋገፍ ማለፍ ባህል እየሆነ መምጣቱን የሚያመላክት ነው ብለዋል።
በ-አክረም ኑርያ












