፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ቀያይ ሰይጣኖቹ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ግብ ጠባቂ ለማስፈረም መወሰናቸውን ዘ ሰን ዘግቧል።
በዘንድሮው የውድድር አመት፣ በተለይም ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ አንድሬ ኦናና የሚፈጽማቸው ስህተቶች ክለቡን ዋጋ እያስከፈሉ ይገኛል።
እሁድ ምሽት በኒውካስትል በተሸነፉበት ጨዋታ ተጫዋቹን ተጠባባቂ በማድረግ ለቱርካዊው ግብ ጠባቂ አልታይ ባይንዲር የመሰለፍ እድል ቢሰጡም የኦናናን ስህተት አስቀጥሏል።
በዚህም ሳቢያ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በክረምቱ ግብ ጠባቂ በአንገብጋቢነት እንደሚያስፈልጋቸው አመላክቷቸዋል።
ራምስዴል ምንም እንኳን ከፕሪምየር ሊግ መውረዱን ባረጋገጠው ሳውዝሃምፕተን የሚጫወት ቢሆንም፣ ችሎታው በበርካታ የሊጉ ክለቦች ተፈላጊ አድርጎታል።
ዩናይትዶች በቀድሞው የአርሰናል ግብ ጠባቂ ላይ ኮስተር ያለ ፍላጎት ያሳዩ ሲሆን ዌስትሃም እና ቼልሲም የተጫዋቹን ፊርማ የሚፈልጉ ቡድኖች ናቸው።
ራምስዴል ከቅዱሳኖቹ ጋር መለያየቱ አርቀሬ ሲሆን መዳረሻው የት ክለብ እንደሚሆን ይጠበቃል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












