:::::::::::::::::::::::::::
በመጀመሪያው ዙር መርሃ ግብር በፒኤስ ጂ 3-1 የተሽነፈው አስቶን ቪላ በሜዳው ቪላ ፓርክ የሚያደርገው የመልስ ጨዋታ ተጠባቂ ሆኗል።
አሰልጣኝ ኡናይ ኢምሬ በፓርክ ደ ፕሪንስ ከደረሰባቸው ሽንፈት በኋላ “ውጤቱን በሜዳችን የመለወጥ ዕድል አለን” ማለታቸው አይዘነጋም።
ቅዳሜ በፕሪምየር ሊጉ ሳውዝሃምፕተንን ያሸነፉት ቪላዎች ቡድናቸው በሙሉ አካላዊ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል።
ቻምፒዮንስ ሊጉን ለማሸነፍ ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው ቡድኖች አንዱ የሆነው ፒኤስ ጂ ወደ ቀጣይ ዙር እንደሚያልፍ ግምት ተሰጥቶታል።
በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ድንቅ ብቃታቸውን ያሳዩት ዴዝሪ ዱዌ እና ክቪችሃ ክቫራትስኬሊሃ በምሽቱ ጨዋታ ተጠባቂ ናቸው። ጨዋታው ምሽት 4 ሰዓት ሲል በቪላ ፓርክ ይጀምራል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












