April 15, 2025
NBC Ethiopia
ሆንግ ኮንግ በተካሄደው የዓለም ቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን ጉባኤ ሀረር ከተማ ያቀረበችው የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል።

የሃረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ሀረር ከተማ የፌደሬሽኑ አባል መሆኗ ከሌሎች ከተሞች ጋር ለማስተሳሰር እና አብሮ ለመስራት እንዲሁም የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል፡፡
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2023 ሀረር የዓለም የቅርስ ከተሞች አባል ሆኗ መመዝገቧ ይታወቃል። የሀረር የማንሰራራት ዘመን ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ መልእክታቸውን አጋርተዋል፡፡
፨
ማስፈንጠሪ (ሊንክ) በመጫን NBC ኢትዮጵያን ይጎብኙ ይወዳጁ ![]()

Source:
NBC Ethiopia
Via:
@NBCEthiopia












