:::::::::::::::::::::::::::::::::::
የሰሜን ለንደኑ ክለብ ፈረንሳዊውን የመሰመር አጥቂ በክረምት ወደ ክለቡ ለማዘዋወር ባየር ሙኒክን ስለመጠየቁ ታውቋል።
የ28 አመቱ ኮማን ምንም እንኳን በተሰጥኦ የተሞላ ቢሆንም፣ የወትሮ አቋሙን አጥቶ ወደ ተጠባባቂ ወንበር ከወረደ ሰንብቷል።
ኮማን ባቫርያኑን በክረምት ለመልቀቅ መወሰኑን ተከትሎ መድፈኞቹ የተጫዋቹ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል።
አርሰናል ባየር ሙኒክን ስለተጫዋቹ ጉዳይ ማነጋገሩን የዘገበው ቢቢሲ፣ የፈረንሳዊው መዳረሻ ሰሜን ለንደን ሊሆን እንደሚችል ገልጿል።
ተጫዋቹ እየቀጠለ ባለው የውድድር አመት የመሰለፍ ዕድል ባገኘባቸው 23 ጨዋታዎች 4 ጎሎችን ሲያስቆጥር፣4 የመጨረሻ ኳስ ለቡድን አጋሮቹ ማድረስ ችሏል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












