ባሳለፍነው አርብ በድንገት ታመው ወደ ሆስፒታል የገቡት አሰልጣኙ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ክለቡ የገለጸ ሲሆን ለቀጣይ ሁለት ጨዋታዎችም ወደ ስራቸው እንደማይመለሱ አስታውቋል።
ኒውካስትል በቀጣይ ከአስቶን ቪላ እና ክሪስታል ፓላስ ጋር በሊጉ በሚኖረው መርሃ ግብር እንደማይገኙ ተነግሯል።
አሰልጣኙ ከሜዳ የሚርቁት ህመሙ ጸንቶባቸው ሳይሆን በተሻለ እረፍት እንዲያደርጉ እና ከቤተሰባቸው ጊዜ እንዲያሳልፉ መሆኑ ተመላክቷል።
እሁድ ዕለት ማንችስተር ዩናይትድን ድል ባደረጉበት ጨዋታም ያልተገኙት የ47 አመቱ ኤዲ ሆው ከሆስፒታል ሆነው ባስተላለፉት መልዕክት ክለቡን እና ተጫዋቾቹን ለሰጧቸው ማበረታቻ አመስግነዋል።
ማክፓይሶቹ በቀጣይ ለሚኖራቸው ሁለት ጨዋታ ምክትል አሰልጣኝ ጄሰን ቲንዴል ቡድኑን ያዘጋጃሉ።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












