:::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
የደቡብ ኮሪያ ጦር እንደገለፀው 10 የሚጠጉ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች የማስጠንቀቂያ ጥይቱ ከተተኮሰ በኋላ ወደ ሰሜን ኮሪያ ተመልሰዋል።
የደቡብ ኮርያ የጦር ሰራዊት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ወታደራዊ ድንበር የሆነውን (MDL) ጥሰው በመግባታቸው ለማስጠንቀቂያ የሚሆን ተኩስ መተኮሱን ጦሩ ገልጿል፡፡
ደቡብ ኮሪያ የሰሜን ኮሪያን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በቅርበት እየተከታተለች እንምትገኝ እና በአሰራር ሂደቱ መሰረት አስፈላጊ እርምጃዎችን እንደምትወስድ ገልፃለች፡፡
ሁለቱ ኮሪያዎች እ.ኤ.አ. ከ1950 እስከ 53 ያደረጉት ጦርነት በሰላም ስምምነት ባለመጠናቀቁ አሁንም ጦርነት ውስጥ ይገኛሉ፡፡
ዘ ስትሬት ታይምስ ዘግቦታል
በ- ሊያ ክብሮም












