Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

“ቀጣይ ወራት ሥራዎችን በጥራት እና በፍጥነት የምናከናውንባቸው ጊዜያት ናቸው” ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

April 8, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች በቀጣይ ወራት የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ዙሪያ እየተወያዩ ነው።

በውይይቱ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይን እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

በውይይቱ መልዕክት ያስተላለፉት ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በዓመቱ የታቀዱ በርካታ ተግባራት መኖራቸውን ገልጸዋል። ተቋማትን ለሚቀጥለው ጊዜ የማዘጋጀት እና የአሥፈጻሚ አካላት ሪፎርም ማድረግ አንደኛው ሥራ መሆኑን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ አሥፈጻሚው አካል የሚመራበት የ25 ዓመታት ዕቅድ መታቀዱንም ገልጸዋል።

የ25 ዓመቱ ዕቅዱ የረጅም እና የመካከለኛ ጊዜ ተልዕኮዎችን ግልጽ ያደረገ መኾኑን ተናግረዋል። የአሥፈጻሚ አካላት አደረጃጀት ምን መኾን መቻል አለበት የሚለው ጥናት መደረጉንም ገልጸዋል።

የፍትሕ አካላትን የሚያቀናጅ፣ የክልሉን ሕዝብ የፍትሕ ጥማት ለማርካት የሚያስችል ሪፎርም እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም የነበረውን ሊያስቀር የሚችል እና የተሻለ ውጤት ሊያስገኝ የሚችል መኾኑንም አንስተዋል።

የጸጥታ አካላት ሪፎርም ሥራ እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል። የጸጥታ ኀይል ሪፎርም ብዙ ጊዜ የወሰደ እና በትኩረት እየተሠራ ያለ መኾኑን ነው የገለጹት። የጸጥታ ኀይሉ ሪፎርሙ በውስጥ ያለውን አቅም እና ሊመጣ የሚችለውን ስጋት ታሳቢ ያደረገ መኾኑንም ተናግረዋል።

የልማት ድርጅቶች ሪፎርም እየተሠራ መኾኑን ነው የገለጹት። የልማት ድርጅቶች ለመንግሥት አቅም መኾን በሚችሉበት መንገድ እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል። የልማት ድርጅቶች ተልዕኳቸውን በለየ መልኩ ሪፎርም መሥራት እንዳስፈለገ ነው ያነሱት።

የልማት ድርጅቶች በምን መልኩ መሥራት እንዳለባቸው ጥናት መጠናቱንም ገልጸዋል። የልማት ድርጅቶችን በቂ የንግድ ልምድ እና አቅም ያለው ሰው እንዲመራቸው ይደረጋል ነው ያሉት።

የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም በትኩረት ሊመራ የሚገባው ጉዳይ መኾኑንም ተናግረዋል። በዓመቱ የማኅበራዊ፣ የምጣኔ ሃብታዊ፣ የፖለቲካዊ ልማት እና የሕግ ማስከበር ሥራዎች መሠራታቸውንም ገልጸዋል።

በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በአገልግሎት ዘርፉ እና በሌሎች ዘርፎች የተሻሉ ሥራዎችን ለመሥራት ተንቀሳቅሰናል ነው ያሉት። የተሻሉ ውጤቶችን ለመፈጸም ጥረት የተደረገበት እንደነበርም ገልጸዋል።

ቀጣይ ወራት በጥራት እና በፍጥነት ሥራዎችን የምናከናውንባቸው ጊዜያት ናቸው ብለዋል። ሥራን በጥራት እና በፍጥነት ለማከናወን መሪን ማጥራት እንደሚጠበቅም አንስተዋል። የተሻለ ሥራ ለመሥራት መሪን ማጥራት በቀጣይም የሚተገበር መኾኑን ነው የተናገሩት። የመንግሥትን የመምራት አቅም ከፍ ማድረግ እና የሕዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ነው የገለጹት።

በቀጣይ ጊዜያት ጠንካራ የፖለቲካ ሥራ መሥራት እንደሚገባም አመላክተዋል። ባለፉት ጊዜያት በተሠራው ሥራ የተደናገረውን ኀይል የመመለስ እና ጽንፈኛ ኀይሉን ይደግፍ የነበረው እውነቱን እንዲረዳ መደረጉን ነው የገለጹት። ከዚህ የተሻለ ሥራ ለመሥራት ሕዝብን ማወያየት እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።

አሁን ያለው ሁኔታ ለአማራ ሕዝብ የማይጠቅም መኾኑንም አመላክተዋል። የአማራ ክልል ሕዝብ ተከታታይ ጉዳት የደረሰበት ሕዝብ ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ከዚህ በላይ እንዳይጎዳ ችግሩን መፍታት ይጠበቅብናል ነው ያሉት።

ወደፊት የሚያራምድ እና አወንታዊ ለውጥ የሚያመጣ የሕግ ማስከበር ሥራ እንደሚሠራም ተናግረዋል። በልማት፣ በመልካም አሥተዳደር እና በሰላም ሥራዎች ላይ ውጤታማነትን ማረጋገጥ ይገባል ነው ያሉት። በተለይ በተመረጡ እና ልዩ ትኩረት በሚሰጣቸው ሥራዎች ላይ ርብርብ ማድረግ ይገባል ብለዋል። በቀጣይ የሚሰጡ ተልዕኮዎችን በንቃት እና በብቃት መወጣት እንደሚገባም አሳስበዋል።ዘገባው የአሚኮ ነው፡፡

ShareTweetShare
Previous Post

የቀድሞ የሊቨርፑል እና የቼልሲ አማካኝ ዮሲ ቤናዩን በእስራኤል በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ላይ ከተሰነዘረው የእጅ ቦምብ ጥቃት መትረፉ ተነግሯል።

Next Post

ደቡብ ኮሪያ ድንበር ጥሰው በገቡ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ላይ መተኮሷን ተናገረች

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ደቡብ ኮሪያ ድንበር ጥሰው በገቡ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ላይ መተኮሷን ተናገረች

ደቡብ ኮሪያ ድንበር ጥሰው በገቡ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ላይ መተኮሷን ተናገረች

የትግራይ ህዝብ ላሳየኝ ክብር እና ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አለኝ – አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ህዝብ ላሳየኝ ክብር እና ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አለኝ - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትራምፕ ዛቻ በቻይና ላይ

የትራምፕ ዛቻ በቻይና ላይ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?