፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የትግራይ ህዝብ ላሳየኝ ክብር እና ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አለኝ ሲሉ የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ።
አቶ ጌታቸው በኤክስ ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው በትግሪኛ ቋንቋ ባሰፈሩት መልዕክት የሁለት ዓመት የጊዜያዊ መስተዳድር ሀላፊነቴን በይፋ አስረክቤያለሁ ብለዋል።
የትግራይ ህዝብ ላሳየኝ ክብር እና ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አለኝ ያሉት አቶ ጌታቸው ህዝባችን ወደ ተሻለ ሁኔታ እንዲመለሰ ሁለንተናዊ ፍላጎቱ እንዲሟላለት የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ ሲሉም ገልጸዋል።
የሰላም እና የለውጥ ፍላጎት እንዳይሰናከል ትግላችንን እናጠናክር በማለትም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡












