፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ ተጨማሪ 50 በመቶ ቀረጥ እንደሚጣል ዝተዋል፡፡
ቻይና ከዚህ ቀደም የተጣለባትን ተጨማሪ ታክስ አስታካ በምትኩ በአሜሪካ ላይ የ34 በመቶ ታክስ በመጣል አፀፋዊ ምላሽ መስጠቷን ተከትሎ ቻይና የጣለችውን ታሪፍ እንድታነሳ አልያም ደግሞ 50 በመቶ ታክስ እንድትከፍል ምርጫ ተሰጥቷል፡፡
ቻይናም በበኩሏ ትራምፕ እንደዛቱት እርምጃ ከወሰዱ ከአሜሪካ ኩባንያዎች ወደ ቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ አጠቃላይ የ104 በመቶ የታክስ ጭማሪ ሊገጥማቸው እንደሚችልም ተናግራለች፡፡ ይህም በሁለቱ የዓለም ታላላቅ ኢኮኖሚ ባለቤቶች መካከል ያለውን ዓለም አቀፋዊ የንግድ ጦርነት የበለጠ ሊያባብሰው ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡
ተጨማሪ ታሪፍ በማውጣት በአሜሪካ ላይ የሚበቀል ማንኛውም ሀገር ወዲያውኑ ከፍተኛ ታሪፍ እንደሚገጥመው ተናግረዋል፡፡ በምትኩም ቤጂንግ ቻይናን መጫን ወይም ማስፈራራት ትክክለኛ መንገድ አይደለም ትላለች፡፡
ትራምፕ ሁለቱም በተከታታይ ታሪፍ ላይ ድርድር ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተናግረዋል። 36 ትሪሊየን ዶላር እዳ እንዳለባቸው ያስታወቁት ፕሬዝዳንቱ አሜሪካ ከሌሎች ሀገራት እና ከቻይና ጋር በመነጋገር ፍትሃዊ ስምምነት ለማድረግ እንደምትፈልግም አስታውቀዋል፡፡ ትራምፕ ባስተላለፉት መልዕክት ከሃገራት ጋር ታሪፍ ላይ የሚደረገው ድርድር በአስቸኳይ መካሄድ እንደሚጀምር አመላክተዋል፡፡
በ-ማህሌት ግርማ












