NBC Ethiopia

ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘቷን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስትር ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ። የሚኒስቴሩ እና ተጠሪ ተቋማቱ አመራሮች የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እየገመገሙ ነው፡፡ በዚሁ ወቅት ሚኒስትሩ፤ በኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፈቃድ ለ2 ነጥብ 6 ሚሊየን ተገልጋዮች አገልግሎት መሰጠቱን እና 2 ነጥብ 2 ሚሊየን የድረ-ፍቃድ ኢንስፔክሽን መከናወኑን ገልጸዋል፡፡

374 ተጨማሪ የሰንበት ገበያዎች ተቋቁመዋል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡ ከወጪ ንግድ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር መገኘቱን ጠቅሰው፤ ይህም በሀገሪቱ ወጪ ንግድ ታሪክ ከፍተኛው ነው ብለዋል፡፡ (ኤፍ ኤም ሲ)
Source:
NBC Ethiopia
Via:
@NBCEthiopia












