ላሊጋውን ከተከታዩ ማድሪድ በ4 ነጥብ ልዩነት በመምራት ላይ የሚገኘው ባርሴሎና በሳምንቱ መጨረሻ በሴቪል ነጥብ እስኪጥል ድረስ በተጋጣሚዎቹ ላይ የበላይነት አለው።
የአሰልጣኝ ሃንስ ፍሊክ ቡድን በጨዋታዎች ላይ ከፍተኛ ግብ በማስቆጠር እና አዝናኝ ጨዋታን በማሳየት ከአውሮፓ ክለቦች በቀዳሚነት ተቀምጧል።
ከፊት መስመር ላይ የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋቾች ራፊኒሃ እና ላሚን ያማል በምሽቱ ጨዋታ ተጠባቂ ሆነዋል።
በቡንደስሊጋው ወደ አውሮፓ ውድድሮች ለመሳተፍ ከሚያስችለው ስፍራ ርቆ 8ተኛ ደረጃ ለይ የተቀመጠው ዶርትሞንድ፣ በቻምፒዮንስ ሊግ ባርሳን የመግጠም ታሪክ ቢኖረውም ማሸነፍ አልቻለም። በምሽቱ ጨዋታ የባርሳ አሸናፊነት በብዙዎች ተገምቷል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












