አዲስ አበባ | ሐምሌ 29 2016| NBC ETHIOPIA-
የምሽት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ወይም ሌት ናይት ሾው በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተቸራቸው እና ተወዳጅነት ያተረፉ ናቸው፡፡
በቴሌቪዥን መስኮት ከሚቀርቡ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች መካከል በርካታ እይታ ያላቸው እና ታዋቂ ከሆኑት መከካል ጥቂቶቹን ልንነግራችሁ ነው፡፡
The Greg Gutfeld Show

The Greg Gutfeld Show ከፈረንጆቹ 2015 እስከ 2021 የአሜሪካን ወግ አጥባቂ ፖለቲከኞች ንግገር ላይ የተመሰረተ እና የሚወጡ ዜናዎችን በመመርኮዝ የሚሰራ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ነው፡፡
ትዕይንቱ ከምሽቱ 4 ሰዓት በፎክስ ኒውስ የሚቀርብ ሲሆን ከ2015 ጀምሮ በግሬግ ጉትፌልድ እየተዘጋጀ ይቀርባል፡፡ከ2016 መጀመሪያ ጀምሮ በቀጥታ ስቱዲዮ በታዳሚ ፊት ለፊት ወቅታዊ ሁኔታዎችን የሚዳስሱ የፖለቲካ ጉዳዮችን በቀልድ እያዋዛ በማቅረብ ተወዳጅነትን አትርፏል፡፡
ከህዳር 2022 ጀምሮ እስከ 2023 መጀመሪያ በአማካይ ወደ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚጠጉ ተመልካቾችን ማፍራት ችሏል፡፡ ይህም በአሜሪካ ከሚታዩ የምሽት ፕሮግራሞች የተሻለ እንዲሆን አስችሎታል፡፡
ከኒውዮርክ በቀጥታ ስቱዲዮ በታዳሚ ፊት ለፊት የሚቀርበው The Greg Gutfeld Show በ COVID-19 ወቅት ከታዳሚ ውጭ ፕሮግራሙ ሲካሄደ ቆይቷል፡፡
ከግንቦት 2022 ጀምሮ ግዙፍ ስቱዲዮን በመገንባት ቀድሞ ከታዳሚዎች ጋር ቆይታ ወደሚያደርግበት ሁኔታ ተመልሷል፡፡
The Graham Norton Show

ሌላኛው ተወዳጅ የምሽት ፕሮግራም The Graham Norton Show ይሰኛል፡፡
በግራሃም ኖርተን ተዘጋጅቶ የሚቀርብ በእንግሊዝ ተወዳጅ አስቂኝ ዘውግ ያላቸው ንግግሮች የማይለዩት ፕሮግራም ነው፡፡ አርብ ምሽት ከሚጠበቁ ፕሮግራሞች ቀዳሚው ሲሆን የኖርተን ችሎታ አጉልቶ ማሳየት ችሏል፡፡
ትዕይንቱ ሲጀምር በሙዚቃ፤ በቀልዶች እንዲሁም ለየት ባለ መልኩ የሚጀመር ሲሆን በአስደሳች አቀራረቡ ተለይቶ ይታወቃል፡፡በዚህም የብሪቲሽ አካዳሚ የቴሌቭዥን ሽልማት ምርጥ የመዝናኛ ፕሮግራም ተብሎ ለሶስት ጊዜ ሽልማቶችን አግኝቷል።
The Graham Norton Show ግርሃም ዊልያም ዎከር የኮሜዲያን ፣ ተዋናይ ፣ ደራሲ እና የቴሌቪዥን አቅራቢነቱን ያንጸባረቀበትም ነው ፡፡
የጉዳዩን ቀጥተኛ ሰው ከማሳተፍ ባለፈ በተለያየ ሙያ ላይ ያሉ ተሳታፊዎችን በማሳተፍ ለየት ያሉ አስተያየቶችን በፕሮግራሙ ያንጸባርቃል፡፡ ይህም ሾውን ለየት ከሚያርጉት ሁኔታዎች ይጠቀሳል፡፡
Last Week Tonight with John Oliver

Last Week Tonight with John Oliver የተሰኘው ፕሮግራም በአዝናኝነቱ ስሟቸው ከሚቀመጡ የምሽት ፕሮግራሞች አንዱ ነው፡፡
በአሜሪካ ከሚቀርቡ የምሽት አስቂኝ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ዋነኛው ነው፡፡ ግማሽ ሰዓት የሚፈጀው ትርኢቱ በፈረንጆቹ 2014 መጨረሻ በቦክስ ኦፊስ የበቃ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም በኦላይን የሚቀርብ ተወዳጅ የምሽት ፕሮግራም ነው፡፡
ትዕይንቱ በሳምንቱ የተከናወኑ ዜናዎችን፣ ፖለቲካዊ እና ወቅታዊ ጉዳዮችን አስተማሪና አስቂኝ በሆነ ዘውግ የሚያቀርብ ነው፡፡ኦሊቨር ከቦክስ ኢፊስ ጋር እስከ 2026 በአየር ላይ መቆየት የሚያችለውን ውልን አራዝሟል፡፡
Bill Maher በHBO

ሪል ታይም ዊዝ Bill Maher በHBO በየሳምንቱ የሚተላለፈው የአሜሪካ ተወዳጅ የምሽት የቴሌቭዥን ሾው ነው፡፡
ፕሮግራሙ የኮሜዲ እና የፖለቲካ እውቀት ባለው ቢል ማሄር ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡በወቅታዊ ጉዳዮች የሚወያዩ እንግዳዎች የሚቀርቡበት ፓናል ሲሆን ከቀደሙት ፕሮግራሞች አንፃር በጉዳዩ ላይ ጥልቅ እውቀቴ ያላቸው እንግዳዎችን ያሳትፋል፡፡
በውይይቱ ጋዜጠኞች፣ ፕሮፌሰሮች እና ፖለቲከኞች እንዲሁም ዘርፈ ብዙ ባለሙያዎች ይሳተፉበታል፡፡ አልፎ አልፎም ጥቂት ተዋናዩች እና ታዋቂ ግለሰቦችን ያሳትፋል፡፡
ትዕይንቱ በHBO የሚቀርብ ሲሆን የሚጋበዙት እንግዶች እና ማሄር በዓለም ፖለቲካ ውስጥ ስለሚታዩት ሁኔታዎች የሚወያዩበት ነው፡፡ በውይይታቸው ተናጋሪው የፈለጉትን ሀሳብ የማቅረብ ነፃነትን የሚያጎናጽፍ ነው፡፡
The Daily Show

ኮሜዲያን፣ ተዋናይ፣ የፖለቲካ ተንታኝ ፣ደራሲ እና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን በማቅረብ ይታወቃል ደቡብ አፍሪካዊ ትሬቨር ኖሃ ።
ከዓለማችን 100 ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች መካከል የሚቀመጠው ትሬቨር ኖሃ የሚያዘጀው ዘዴሊ ሾው በምሽት ከሚቀርቡ ፕሮግራሞች ተወዳጁ ነው፡፡
ደቡብ አፍሪካዊ ትሬቨር ኖሃ ጥቁር መሆኑ ጫና ሳያሳድርበት በኮሜዲ ስራው ጠንከር ያሉ ጉዳዮችን ማቅረብ መገለጫው ነው፡፡
በ2015 በኮሜዲ Jon Stewart ይመራ የነበረዉ”The Daily Showን” ኖሃ በመዉሰዱ ምርጥ የቴሌዥን ሾው አቅራቢ ና አዘጋጅ በመሆን በአሜሪካ ብሎም በመላው ዓለም ተወዳጅ ሆኗል፡፡
በየጊዜዉ በሚያቀርባቸዉ አዝናኛ ና ገሳጭ የመድረክ ስራዎቹ ዝነኝነቱ እንዲያይል አድርጎታል፡፡ አለምቀፍ ሁነቶች ወደ መድረክ በማቅረብ በትችትና አዝናኝ በሆነ መልኩ ማቅረብ መለያዉ ነዉ፡፡
በዴሊ ሾዉ አስቂኝ ዘዉግ ያላቸዉ ፕሮግራሞችን ቢያቀርብም ጠንካራ ሀገራዊ ጉዳዮችን እንዲሁም ዓለምን የሚዘዉሩትን የበለፀጉ አገራትንም ጭምር በቀልድ እያዋዛ መገሰጹም ልማዱ ነዉ፡፡
በተለይ ቀለምን መሰረት ያደረጉ ጭቆናዎች በስራዎቹ ሰፊ ትኩረት የሚሰጣቸው እና በሳቅ እያዋዛ በመተቸት ያቀርባል፡፡












