፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 29 2016| NBC ETHIOPIA- ዩክሬን የአሜሪካ ስሪቱን F-16 የጦር ጀት ለጦርነት ማሰናዳቷን አስታውቃለች ፡፡
የዩክሬን አብራሪዎች ያንን የኤፍ -16 የጦር ጀት ከዚያው በዩክሬን ምድር ሳይወጡ ባሻቸው መጠን እያበረሩት ታይተዋል፡፡
የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ቨሎዲሚር ዘለንስኪ በሰጡት መግለጫ ለሀያ ዘጠኝ ወራት ደጅ የተፀናበት የአሜሪካ ስሪቱ የኤፍ -16 የጦር ጀት ከእጃችን ገብቶ አብራሪዎቻችንም በተገቢው ሰልጥነው ከዚህ በኃላ በቀጥታ ከጥቅም ላይ ይውላል ነው ያሉት፡፡

የሩሲያ ባለስልጣናት በበኩላቸው በሰጡት ማብራሪያ የነዚያ የኤፍ -16 የጦር ጀቶች መምጣት ስጋታቸው እንዳልሆነ እና በቀጥታም እየመቱ እንደሚጥሏቸው ነው የዛቱት ፡፡
የኤፍ -16 የጦር ጀቶች ባለ ሃያ ሚሊ-ሜትር ጠመንጃ ቦምቦችን ፣ ሮኬቶችንና ሚሳይሎችን ተሸክመው በአየር ላይ ጥቃት ውጤታማ እንደሆኑ ይነገራል ዘገባው የኤን ቲዲ ነው፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv



See insights
Boost a post
Like
Comment
Send
Share












