፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 29 2016| NBC ETHIOPIA-በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት የተግባራት አፈፃፀም ግምገማ እና የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ ትውውቅ መድረክ በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ላይ በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ ፣ በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ዘሪሁን ፍቅሩ፣ በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍስሃ ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎች የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር የፖርቲ አመራሮች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ እንደተናገሩት፣ ከላይ እስከ ታች የሚገኘውን የፖርቲ መዋቅርን በማጠናከር ተግባራትን በመናበብ ፣ በቅንጅት እና በማስተሳሰር በውጤታማነት መምራት የሞት የሽረት ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።
የፓርቲው መዋቅር ሚናው ከፍ ያለ ነው ያሉት ኃላፊው፣ መዋቅሩ እንደአስኳል ሁኖ ሁሉንም ተግባራት የመምራት እና የማስተሳሰር ኃላፊነትን በማጠናከር የፖለቲካ ስራዎችን በላቀ ትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
በሁሉም ተግባራት የላቀ ውጤት ለማስመዝገብም በሁሉም እርከኖች ግልጽ ውይይት እና መግባባት እንደሚጠይቅም ጨምረው ተናግረዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












