Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Uncategorized

“እንደ መሪ በየደረጃው ያለን አመራሮች በክልላችን ጉዳይ ኃላፊነት መውሰድ አለብን” ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

August 5, 2024
in Uncategorized
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ 

አዲስ አበባ | ሐምሌ 29 2016| NBC ETHIOPIA-በየደረጃው ያሉ የአማራ ክልል ከተማ ልማት ዘርፍ ተቋማት በማክሮ ኢኮኖሚ የትኩረት ጉዳዮች ዙሪያ እየመከሩ ነው።

በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የሥራ እድል ፈጠራ እና የኑሮ ውድነትን መቀነስ የበጀት ዓመቱ የትኩረት መስክ ናቸው ብለዋል።

የስራ እድል ፈጠራም ሆነ የኑሮ ውድነት ቅነሳ ስለምንመኘው ብቻ የሚመጣ አይደለም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የመሪነት ሚናችን እና የሕዝብ ተቆርቋሪነታችን የሚገለጥበት ብርቱ ጥረትን ይጠይቃል ነው ያሉት። በተለይም የፖለቲካ መሪው ሊመራበት ይገባል ያሉትን የሥራ መርህ በዝርዝር አስቀምጠዋል

መሪነታችሁ ከግብረ ገብነት እና ከሥነ ምግባር የመነጨ ሊሆን ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ቅቡል ባሕሪ እስካለን ድረስ የምንመራው ሕዝብ የነገርነውን የሚሰማ እና ለተግባራዊነቱም የሚተባበር ይሆናል ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው የፖለቲካ አመራሩ ቁርጠኛ፣ ታታሪ እና ለሕዝብ ጥቅም የሚቆረቆር መሆን እንዳለበት ጠቁመው “እንደ መሪ በየደረጃው ያለን አመራሮች በክልላችን ጉዳይ ኃላፊነት መውሰድ አለብን” ነው ያሉት። ለሚፈጠር ችግር ባለቤት ከመፈለግ እና በድህረ ችግር ትንታኔ ከመጠመድ ወጥቶ በኀላፊነት መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የክልሉ መሠረታዊ ችግሮች የሚመነጩት ከምጣኔ ሃብታዊ ችግሮች ነው። ምጣኔ ሃብታዊ ችግሮቻችን ለመሻገር ሃብት መፍጠር ያስፈልጋል ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ንግድ፣ ትራንስፖርት፣ ቱሪዝም እና ቴክኖሎጂን ማቀናጀት ያስፈልጋል ብለዋል። ገቢ የመሰብሰብ ጉዳይም በቀጣይ ዓመት በትኩረት የሚፈጸም ጉዳያችን ነው ብለዋል።

ሃብት ከማሰባሰብ ባሻገር ከእለት ፍጆታ የተሻገረ  ሃብት ማከማቸት ላይ አቅዶ መሥራት እንደሚያስፈልግም አንስተዋል። ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ፍልሰትን እና የከተሞችን መስፋፋት (ክትመትን) በአግባቡ መምራት ይኖርብናል ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ፤ የተገራ እና መጻዒውን ጊዜ ታሳቢ ያደረገ ክትመትን አውን እናድርግ ብለዋል።

ሰላም እና ጸጥታን ማስከበር ሌላው ትኩረት መሰጠት ያለበት ጉዳይ እንደሆነም አንስተዋል። በቀጣይ ጊዜያት ለአመራሩ አፈጻጸም ላይ የተመሠረተ ተጠያቂነት እና እውቅና እንደሚኖርም አንስተዋል። የሥራ እድል ፈጠራ እና ድህነት ቅነሳ ደግሞ አመራሩ የሚለካባቸው ቁልፍ ጉዳዮች ስለመሆናቸው ማንሳታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

📌YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC

📌 TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia

📌Website – https://nbcethiopia.com/news/

📌Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc

#NBC_ETHIOPIA

#ሆኖ_መገኘት

ShareTweetShare
Previous Post

ተወዳጅነትን ያተረፉ የምሽት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች

Next Post

“የፓርቲ መዋቅርን በማጠናከር ተግባራትን በመናበብ፣ በቅንጅት እና በማስተሳሰር መምራት የሞት የሽረት ጉዳይ ነው”-አቶ ይርጋ ሲሳይ

Related Posts

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ
News

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ

November 13, 2026
16
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Uncategorized

የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

October 10, 2026
19
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል
News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

October 9, 2026
16
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ
News

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

October 8, 2026
33
የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ
News

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

October 2, 2026
23
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019
Uncategorized

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019

September 27, 2026
23
Next Post
“የፓርቲ መዋቅርን በማጠናከር ተግባራትን በመናበብ፣ በቅንጅት እና በማስተሳሰር መምራት የሞት የሽረት ጉዳይ ነው”-አቶ ይርጋ ሲሳይ

"የፓርቲ መዋቅርን በማጠናከር ተግባራትን በመናበብ፣ በቅንጅት እና በማስተሳሰር መምራት የሞት የሽረት ጉዳይ ነው"-አቶ ይርጋ ሲሳይ

ዩክሬን F-16 የጦር ጀቶችን ጥቅም ላይ ልታውል ነው

ዩክሬን F-16 የጦር ጀቶችን ጥቅም ላይ ልታውል ነው

የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ማስጠንቀቅያ

የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ማስጠንቀቅያ

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?