፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 30 2016| NBC ETHIOPIA-የፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ ለሆነው የጽዱ ኢትዮጵያን ንቅናቄን በመቀላቀል የ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ውብና ዘመናዊ ከተማ ለመፍጠር የሚደረገውን አገራዊ ጥረት የሚያግዙ በርካታ ሥራዎችን እያከናወነም ነው ፡፡
በሚገነባቸው ዘመናዊ ሕንጻዎችና የመኖሪያ መንደሮች ውበትን ፣ጥራትንና እና ዘመናዊነት ታሳቢ ያደረጉ ግንባታዎች እንዲሆኑ በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ለጽዱ ኢትዮጵያ ንቅንናቄ መሰል ድጋፎቹን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል፡፡
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ታሳቢ በማድረግ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












