፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 30 2016| NBC ETHIOPIA-እንደ ፌስታል ያሉ አካባቢን የሚበክሉ ፕላስቲኮችን ማምረት ወንጀል መሆኑን የገለጸው ባለስልጣኑ በድብቅ የሚያመርቱ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።
ከኢንዱስትሪና ከተማ መስፋፋት እንዲሁም ከህዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ በከተማዋ ከፍተኛ ብክለት መኖሩን በተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ የአየር ብክለት መለኪያ መሳሪያዎቹ የሚያገኘው መረጃ እንደሚያመለክት ባለስልጣኑ ገልጿል።

የአካባቢ ፖሊሲ ማዕቀፉ ዜጎች በንፁህና ጤናማ አካባቢ የመኖር መብት እንዳላቸው ቢደነግግም ድምፅን ጨምሮ የመዲናዋ ነዋሪዎች በተለያዩ ብክለቶች እየተቸገሩ ስለመሆናቸው ተነግሯል።
ባለስልጣኑ “ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ” በሚል የ6 ወራት የአካባቢ ብክለት ንቅንቄ እያካሄደ ይገኛል። በዛሬው ዕለትም በፕላስቲክ ብክለት ዙሪያ ለኪነ-ጥበብና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር አካሂዷል።
በ-መቅደስ ደምስ
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












