፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 18፣ 2016| NBC ETHIOPIA- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲስተም ማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም በሂሳብችሁ ከተቀመጠ ገንዘብ ውጭ በሕገወጥ መንገድ ገንዘብ የወሰዳችሁ ግለሰቦች በፈቃደኝነት ሂሳባችሁ በሚገኝበት ቅርንጫፍ በመቅረብ ወይም ዲጂታል የክፍያ ዘዴን በመጠቀም ገንዘቡን እስከ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም ተመላሽ የምታደርጉበትን ዕድል ባንካችን ማመቻቸቱ ይታወቃል።
በዚህ መሰረት 9 ሺህ 281 የሚሆኑ ግለሰቦች በተሰጠው ጊዜ ተጠቅመው የወሰዱትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ መልሰዋል፡፡
ሆኖም 5166 ግለሰቦች ባንኩ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ በከፊል ተመላሽ አድርገዋል ቢሆንም ቀሪውን ገንዘብ ተመላሽ አላደረጉም ፡፡
ባንኩ ቀደም ሲል ባስጠነቀቀው መሠረት ወደ ቀጣዩ ሕጋዊ እርምጃ ከማለፉ በፊት ቀሪውን ገንዘብ ተመላሽ እንዲያደርጉ ተጨማሪ ዕድል የሰጠ ሲሆን እስከ ቅዳሜ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ ገንዘቡን ተመለሽ እንዲያደርጉ እና ነገር ግን እስከ ተጠቀሰው ቀን ገንዘቡን የማይመልሱ ካሉ ግን በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘዴዎችን በመጠቀም ሙሉ ስማችሁን፣ ፎቷችሁን፣ በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ በመውሰድ ወንጀል መጠርጠራችሁን ተጠቅሶ ለሚመለከታቸው የሕግ አካላትና ተቋማት በማሳወቅ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ ፤ እንዲሁም ከሕግ አካላትና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር ቀጣይ የወንጀል፣ የፍትሐ ብሔርና የአስተዳደር ሕጋዊ እርምጃዎች እንደሚወሰድባችሁ ለመጨረሻ ጊዜ አሳስቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












