አዲስ አበባ | መጋቢት 18፣ 2016| NBC ETHIOPIA- አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የግጭት እና ማረጋጋት ሥራዎች ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ኤን ዊኮክሲ ጋር ተወያዩ::
-በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 7 ሚሊየን ሄክታር አፈርና 3.1 ሚሊየን ሄክታር መሬት በጠንካራ አሲድ መጠቃቱን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
-46 ሺህ የሠላም በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ በ”በጎነት ለአብሮነት” መርሃ ግብር ስልጠና ወስደው አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ የሠላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
-የሀረር ቁጥር 4 ባለ 400 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክትን ለማስጀመር የሚያስችሉ የዝግጅት ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸው ተጠቆመ፡፡
-ከ2013 እስከ 2015 በጀት ዓመት 296 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሥራ ክንውንና የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርት አለማቅረባቸውን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አስታወቀ።
– ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ሥራ ሂደት መገምገማቸውን ገልጸዋል።
-የአንበሳ እና ሸገር ከተማ አውቶቡሶች የመገልገያ ትኬት ከነገ ጀምሮ የሚቀየር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












