አዲስ አበባ | መጋቢት 18፣ 2016| NBC ETHIOPIA-ዩክሬን ሩሲያን ለመመከት የሚያስችላትን በሀገሯ ውስጥ ለሚሠሩ የጦር መሣሪያዎች የምታወጣውን ወጪ ከፍ ማድረጓን አስታወቀች፡፡
ዩክሬን በፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኘውን የመከላከያ ኢንዱስትሪዋን በገንዘብ በመደገፍ ፤ በቤት ውስጥ የሚሰሩ የጦር መሳሪያዎች እና ጥይቶች በብዛት በማምረት ከሩሲያ ጋር ለምታደርገው ጦርነት ይረዳል ሚል ተስፋ እንዳላትም ተመላክቷል ።
ባለፈው ዓመት አሜሪካ እና አውሮፓ የሩሲያን ጦር በመቃወም የጦር መሳሪያዎችን እና ሌሎች ዕርዳታዎችን ወደ ዩክሬን በከፍተኛ ደረጃ ሲልኩ እንደነበር ይታወሳል፡፡
አሁን ላይ ለጋሽ ሀገራት ለዩክሬን የሚያደርጉትን እገዛ መቀነሳቸውን ተከትሎ ይመስላል የዩክሬን መንግስት በፈረንጆቹ 2024 1.4 ቢሊዮን ዶላር በመበጀት የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎችን ማስፋፋት የፈለገችው ተብሏል፡፡ ዘገባው የቲ አር ቲ ወርልድ ነው ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












