Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Health

የወር አበባ ጊዜ ህመም (DYSMENORRHEA)

March 28, 2024
in Health
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አዲስ አበባ | መጋቢት 19፣ 2016| NBC ETHIOPIA-የወር አበባ ጊዜ ህመም (Dysmenorrhea) ማለት ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ህመም ሲሆን፤ በብዛት የሆድ ቁርጠት እና የወገብ (የታችኛው ጀርባ) ህመም ስሜት አለው። በአንዳንዶች ላይ የታፋ ህመም ፣ ተቅማጥ፣ የማቅለሽለሽ ስሜት፣ ማስመለስ፣ ራስ ምታት እና ድካም ምልክቶች ሊኖሩት ይችላል።

የወር አበባ ከሚያዩ ሴቶች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በየወሩ ከ 1 እስከ 2 ቀን ድረስ ሕመም ያጋጥማቸዋል። አብዛኛውን ጊዜ ሕመሙ የበዛ ነው። ይሁን እንጂ ለአንዳንድ ሴቶች ይህ ሕመም በጣም ከባድ ከመሆኑ የተነሳ በወር ውስጥ ለበርካታ ቀናት የተለመደውን እንቅስቃሴያቸውን እንዳያከናውኑ ይከለክላቸዋል።

ሁለት አይነት የወር አበባ ጊዜ ህመም አሉ እነሱም፦

• ከበሽታ ጋር ያልተያያዘ የወር አበባ ጊዜ ህመም (Primary Dysmenorrhea)

• ከበሽታ ጋር የተያያዘ የወር አበባ ጊዜ ህመም (Secondary Dysmenorrhea)

1.ከበሽታ ጋር ያልተያያዘ (Primary Dysmenorrhea) የሚከሰተው ፕሮስታግላንዲን በተባሉ ከማህፀን ግድግዳ ላይ ባሉ ተፈጥሯዊ ኬሚካሎች ምክንያት ነው። እነዚህ ኬሚካሎች (ፕሮስታግላንዲኖች) የማህፀን ጡንቻዎችና የደም ሥሮች እንዲኮማተሩ ያደርጋሉ። ‍ይህ መኮማተር ለህመሙ መንስኤ ይሆናል። የእነዚህ ፕሮስታግላንዲኖች (ኬሚካሎች) መጠን የወር አበባ የመጀመሪያ ቀናት ላይ ከፍተኛ ስለሆነ ሕመሙም ከፍተኛ ነው። የደም መፍሰስ እየቀጠለና የወር አበባ እየፈሰሰ ሲሄድ የፕሮስታግላንዲኖች መጠን ይቀንሳል። ሕመምም ከመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት በኋላ የሚቀንሰው ለዚህ ነው። ይህ የወር አበባ ጊዜ ህመም የሚጀምረው አንዲት ልጅ የወር አበባ ማየት ከጀመረች ብዙም ሳይቆይ ነው። ብዙ ሴቶች ዕድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ የወር አበባ ጊዜ ህመም እየቀነሰ ይመጣል። ይህ ዓይነቱ ሕመም ከወሊድ በኋላም ሊሻሻል ይችላል።

2.ከበሽታ ጋር የተያያዘ (Secondary Dysmenorrhea) የሚከሰተው በመራቢያ አካላት ላይ በሚከሰት የጤና እክል ምክንያት ነው። ሕመሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የሚሄድ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ከተለመደው የወር አበባ ቁርጠት የበለጠ ጊዜ ይቆያል። በተጨማሪም ሕመሙ የሚጀምረው የወር አበባ ከመጀመሩ ከጥቂት ቀናት በፊት ሊሆን ይችላል። ሕመሙ እየተባባሰ ሊሄድና የወር አበባ መፍሰስ ካቆመ በኋላ ላይጠፋ ይችላል።

የወር አበባ ጊዜ ህመም እንዴት ማከም እንችላለን?

የወር አበባ ጊዜ ህመም እንዴት ማከም እንችላለን?

የወር አበባ ጊዜ ህመምን በርካታ የቤት ውስጥ ዘዴዎች ፣ የሕመም ማስታገሻ እና የሆርሞን ህክምና(hormonal therapy) በመጠቀም ማከም ይቻላል፡፡

የቤት ውስጥ ማከምያ ዘዴዎች

1. ሙቀት- በታችኛው ሆድ ላይ ማሞቂያ ፓድ ወይም ሙቅ ውሃ የያዘ ጠርሙስ በመጠቀም ማሞቅ ህመምን በእጅጉ ሊቀንስ ይችላል። የሕመም መቀነስ አቅሙም ከማስታገሻ መድሃኒት ጋር ተወዳዳሪ ሲሆን የማስታገሻ መድሃኒት እና ሙቀትን በጋራ መጠቀም የበለጠ ህመም የማጥፋት አቅም አለው። በጣም ሞቃት በሆነ የማሞቂያ ፓድ ወይም ትኩስ የውሃ ጠርሙስ ቆዳን ከማቃጠል መቆጠብ አስፈላጊ ነው፤ በግምት 40ºC (ለሰስ ያለ) ሙቀትን መጠቀም ይመከራል። ሙቀቱ አስፈላጊ ሆኖ በሚታሰብበት ጊዜ ሁሉ ልንጠቀመው እንችላለን።

2. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ- በሳምንቱ ውስጥ አብዛኛውን ቀን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ጥሩ ስሜት እንዲሰማን ከማድረግ ባለፈ ሕመምን የሚያግዱ ኬሚካሎችን ለማምረት ይረዳል። ለዚህም እንደ መራመድ፣ የሶምሶማ ሩጫ ፣ ሳይክል መንዳት ወይም መዋኘት የመሳሰሉት የኤሮቢክስ እንቅስቃሴዎች ይመከራሉ።

3. እንቅልፍ- ከወር አበባ በፊትና ወቅት በቂ እንቅልፍ መተኛት አስፈላጊ ነው። ጥሩ እረፍት ማግኘት የወር አበባ ጊዜ የሚያጋጥምን ህመም ለመቋቋም ሊረዳ ይችላል።

የሕመም ማስታገሻ መድሀኒቶች

• የሕመም ማስታገሻ መድሀኒቶች (NSAIDs)-ህመምን እና ትኩሳትን የሚቀንሱ መድሃኒቶች ሲሆኑ፤ ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ሕመምን በመቀነስ ረገድ በጣም ውጤታማ የሆኑ መድኃኒቶች ናቸው። አንዳንድ የሕመም ማስታገሻ መድሀኒቶች (NSAIDs) ያለ ሐኪም ማዘዣ መገኘት ይችላሉ፤ ከእነዚህም አይቡፕሮፌን(Ibuprofen) በዋናነት ይጠቀሳል። እነዚህ መዳኒቶች (NSAIDs) የደም መፍሰስ ወይም ሌሎች የወር አበባ ምልክቶች እንደጀመሩ ወይም ከጀመሩ ከሁለት እስከ ሦስት ቀናት ባለ ጊዜ በቋሚ ፕሮግራም ከተወሰዱ በጣም ውጤታማ ናቸው ። የደም መፍሰስ ችግር፣ አስም፣ አስፕሪን አለርጂ፣ የጉበት ጉዳት፣ የኩላሊት ጉዳት፣ የአንጀት ቁስል፣ የጨጓራ ቁስል እና የመሳስሉት ተያያዥ በሽታ ያለባቸው ሰዎች እነዚህን የሕመም ማስታገሻ መድሀኒቶች (NSAIDsን) መውሰድ የለባቸውም። በተጨማሪም ስለ የወር አበባ ጊዜ ህመምን ማስታገሻ ጉዳይ ሃኪም ማማከር ይኖርባችዋል።

የሆርሞን ህክምና (hormonal therapy) 

• የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች (ኪኒኖች) እና ሌሎች የሆርሞን የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች (ለምሳሌ፡ መርፌ፣ ሉፕ (IUD) እና የቆዳ ስር የሚቀመጠው የወሊድ መከላከያ (ኢምፕላንት) የወር አበባ ጊዜ ህመም ላላቸው ሴቶች ውጤታማ ህክምናዎች ናቸው። እነዚህ መድሀኒቶች ፕሮስታግላንዲንን (ማህፀን እንዲኮማተር የሚያደርገው ኬሚካል) የሚያመርተው የማህፀን ግድግዳ በመቀነስ ሕመም፣ ቁርጠትና የወር አበባ መፍሰስ እንዲቀነስ ያደርጋሉ። ይህ ዘዴ በተለይ እርግዝናን መከላከል ለሚፈልጉ ሴቶች በጣም ጠቃሚ ነው ። ነገር ግን የወሲብ ግንኙነት የማያረጉ ሴቶችም ሊጠቀሙበት ይችላሉ። አብዛኛውን ጊዜ የሆርሞን የወሊድ መቆጣጠሪያ ህክምናን ከሁለት እስከ ሶስት ወር ከተጠቀሙ በኋላ ከፍተኛ ለውጥ ይኖራቸዋል።

• ሉፕ (IUD)- ሌቭኖርገስትሬል (ሚሬና) የተባለውን ሆርሞን የያዘው ሉፕ (IUD) ከላይ እንደተጠቀሱት የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች እና ሌሎች የሆርሞን የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች የወር አበባ ጊዜ ህመምን 50 በመቶ ሊቀንስ ይችላል።

በተጠቀሱት ዘዴዎች ሕመሙ በበቂ ሁኔታ ካላስታገሰ ምን ማድረግ እንችላለን?

1. የወር አበባ ጊዜ ህመም በጣም ውጤታማ የሆኑ ህክምናዎች የሕመም ማስታገሻ መድሀኒቶች(NSAIDs) ፣ የወሊድ መቆጣጠሪያ ኪኒኖች እና ሌሎች የሆርሞን የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች ናቸው። ከእነዚህ የሕክምና ዓይነቶች አንዱ በሁለት ወይም በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ሕመሙን በበቂ ሁኔታ ካላስታገሰው ሌላ ሕክምና ሊሰጥ ይችላል። ለምሳሌ ያህል አንዲት ሴት የሕመም ማስታገሻ መድሀኒቶች (NSAIDs) ሞክራ የወር አበባ ጊዜ ህመም ካልታገሰ፣ በሕመም ማስታገሻ መድሀኒቶች ምትክ ወይም በተጨማሪ የሆርሞን የወሊድ መቆጣጠሪያ ልትወስድ ትችላለች።

2. ከላይ የተጠቀሱት መንገዶች ሕመሙን በሚገባ ካላሻሻሉ ቀጣዩ እርምጃ ከበሽታ ጋር የተያያዘ (Secondary Dysmenorrhea) ሊሆን ስለሚችል የወር አበባ ጊዜ ህመም መንስኤዎችን መመርመር እና ማከም ነው። ለዚህም ህክምና ቦታ በመሄድ ተገቢውን ምርመራ እና ህክምና ማግኘት ተገቢ ነው።

ShareTweetShare
Previous Post

ዩክሬን በሀገሯ ውስጥ ለሚሠሩ የጦር መሣሪያዎች የምታወጣውን ወጪ ከፍ አደረገች

Next Post

“ለቤን ዋይት አሁንም በራችን ክፍት ነው” አሰልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት

Related Posts

⁨አዲስ ጥናት! _የማህበረሰብ ልማት ባለሞያ ዘላለም ይትባረክ! _NBC ቅዳሜ
Health

⁨አዲስ ጥናት! _የማህበረሰብ ልማት ባለሞያ ዘላለም ይትባረክ! _NBC ቅዳሜ

June 15, 2026
38
በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም እየሆኑ ነው
Health

በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም እየሆኑ ነው

June 4, 2026
24
⁨ሞት መድሃኒት አለዉ | ቆንጆ አለመሆኗ ሂዎቷን አመሰቃቅሎታል | ለራሳቸው መሆን የከበዳቸዉ ብዙ የህክምና ባለሙያውች አሉ | NBC ቅዳሜ
Health

⁨ሞት መድሃኒት አለዉ | ቆንጆ አለመሆኗ ሂዎቷን አመሰቃቅሎታል | ለራሳቸው መሆን የከበዳቸዉ ብዙ የህክምና ባለሙያውች አሉ | NBC ቅዳሜ

March 16, 2026
85
“ዳውን ሲንድረም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ስጦታ ነው!” | ውሎ በዲቦራ ፋውንዴሽን | በNBC እሁድ
Health

“ዳውን ሲንድረም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ስጦታ ነው!” | ውሎ በዲቦራ ፋውንዴሽን | በNBC እሁድ

February 17, 2026
48
ጥራቱ ያልጠበቀ ምርትን ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ
Health

ጥራቱ ያልጠበቀ ምርትን ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ

January 21, 2026
42
ወላጆች ስለ ልጆቻችችሁ ቶንሲል ግዴታ ማወቅ ያለባችሁ ነግሮች | ከታዋቂው የአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር | NBC ጤና
Health

ወላጆች ስለ ልጆቻችችሁ ቶንሲል ግዴታ ማወቅ ያለባችሁ ነግሮች | ከታዋቂው የአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር | NBC ጤና

August 25, 2025
89
Next Post
“ለቤን ዋይት አሁንም በራችን ክፍት ነው” አሰልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት

"ለቤን ዋይት አሁንም በራችን ክፍት ነው" አሰልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት

አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

አይረሴው የፊልም ተዋናይ ጃኪ ቻን

አይረሴው የፊልም ተዋናይ ጃኪ ቻን

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?