አዲስ አበባ | መጋቢት 18፣ 2016| NBC ETHIOPIA- በቱኒዚያ እ.ኤ.አ. በ2013 የተቃዋሚ ፖለቲከኛ መሪ ቾክሪ ቤላይድን በመግደል ተይዘው የነበሩ አራት ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ አስተላለፈች ተባለ ።

እ.ኤ.አ. በ2011 የፕሬዝዳንት ቤን አሊን መንግስት በሕዝባዊ አመጽ መውረድን ተከትሎ የተገደለው ተቃዋሚ መሪ ግድያ በሀገሪቱ ላይ ብትብጥ አስከትሎ እንደነበር ሚታወስ ሲሆን፤ የቱኒዚያ ፍርድ ቤት ከ11 ዓመት በፊት በተገደለው በቾክሪ ቤላይድ፤ ግድያ በፈጸሙ አራት ሰዎች ላይ በሞት እንዲቀጡ እና ሌሎች ሁለቱ ሰዎች ደግሞ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲታሰሩ ወስኗል ተብሏል፡፡
እንደ አልጀዚራ ዘገባ በአጠቃላይ 23 ሰዎች ከግድያው ጋር በተያያዘ ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን በሌሎች ተከሳሾች ላይ ከሁለት እስከ 120 ዓመት የሚደርስ የቅጣት ውሳኔ ሲተላለፍ 5ቱ ክሳቸው ተቋርጧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












