፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 18፣ 2016| NBC ETHIOPIA- የግብርና ሚኒስቴር አሲዳማ አፈርን በኖራ በማከም ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያግዝ ምክክር እያከናወነ ይገኛል። በምክክሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን፣ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢ/ር ሃብታሙ ተገኝ ጨምሮ ሌሎች የባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በውይይቱ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 7 ሚሊየን ሄክታር አፈር በአሲድ መጠቃቱን ገልፀው 3.1 ሚሊየን ሄክታር መሬት በጠንካራ አሲድ እንደተጠቃ አስታውቀዋል።
የአፈር ጤንነትን በጠበቅ ረገድ ክፍተቶች በመኖራቸው፤ ኦሮሚያ፣አማራ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ያሏቸው መሬቶች በጠንካራ አሲዳማ አፈር የተጠቁ መሆናቸው ተገልጿል።
የግብርና ምርት እና ምርታማነት በእጅጉ እየጎዳ የሚገኘው የአፈር አሲዳማ መሆንን ለመከላከል የግብርና ኖራን መጠቀም አምራጭ መሆኑን በግብርና ሚኒስቴር የኢንቨስትመንት ግብአት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) በውይይት መድረኩ አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ከ9መቶ ሚሊየን ቶን በላይ የኖራ ድንጋይ ሀብት ያላት ሲሆን ከ20 በላይ የሲሚንቶ እና የኖራ አምራች ኢንዱስትሪዎች በዓመት 1.1 ሚሊየን ቶን የግብርና ኖራ እንደሚያመርቱ ተገልጿል።
የኖራ ድንጋይ ሀብት ምንም እንኳን በሀገሪቱ ከፍተኛ ቢሆንም አርሶ አደሩ ኖራን እንዲጠቀም ለማስቻል በተመጣኝ ዋጋ ከማቅረብ አንፃር ክፍተቶች መኖራቸው ተመላከቷል።
በ2016/17 የምርት ዘመን 100 ሺህ ሄክታር አሲዳማ አፈርን ለማከም እንደሚሰራ በመርሐ ግብሩ የተገለጸ ሲሆን 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ግቡን ማሳካት ተዘጋጅቷል ተብሏል፡፡
አሲዳማ አፈርን በኖራ በማከም ምርታማነትን ማሳደግን ታሳቢ ያደረገ መርሐ ግብር ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት “የአፈር ጤና ለሀገር ህልውና” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ ያለው።
በ-ሀሴት ኃይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












