አዲስ አበባ | የካቲት 28፣ 2016| NBC ETHIOPIA -ነገ ምሽት በሳውዲ የሚካሄደው የአንቶኒ ጆሹዋና ፍራንሲስ ንጋኑ የከባድ ሚዛን ቡጢ ፍልሚያ በጉጉት ይጠበቃል።
በሪያድ ኪንግደም አሬና የሚካሄደው ወሳኙና ተጠባቂው ፍልሚያ በ10 ዙሮች እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።
እንግሊዛዊው የቀድሞ የሁለት ጊዜያት የ”ዩኒፋይድ ክብር” (WBA, WBC& IBF) አሸናፊው አንቶኒ ጆሹዋ 50 ሚሊዮን ፍሬንች – ካሜሮናዊው ንጋኑ ደግሞ 20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት እንደሚወስዱ ተነግሯል።

የአሜሪካው ሚክስድ ማርሻል አርት አወዳዳሪ (UFC) የቀድሞ ተፋላሚ የነበረው ንጋኑ ቡጢ ስፖርትን የሙሉ ጊዜ ስራው ካደረገ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ የሚያደርገው ፕሮፌሽናል ግጥሚያው ነው።
ከአራት ወራት በፊት የመጀመሪያ ፍልሚያውን በሪያድ ኪንግደም አሬና ከሌላኛው እንግሊዛዊ የከባድ ሚዛን ንጉስ ታይሰን ፊዩሪ ጋር አድርጎ በተከፋፈለ አወዛጋቢ የዳኛ ዉሳኔ በጠባብ የነጥብ ልዩነት መሸነፉ ይታወሳል።
የበኩር ግጥሚያውን በሽንፈት ይደምደም እንጅ እስካሁን አንድም ሽንፈት የማያውቀው ፊዩሪን ገና በ5ኛው ዙር መሬት ላይ በመዘረር ዓለምን አስደምሟል።
አንቶኒ ጆሹዋ በበኩሉ፣ በዩክሬናዊው ኦሌክሳንደር ኡሲክ በተከታታይ ሁለት ጊዜ ከደረሰበት ሽንፈት በኋላ ያደረጋቸውን 3 ግጥሚያዎች እንደማሸነፉ በጥሩ መነቃቃት ላይ ይገኛል። በዕለቱ ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ ምድቦች በርካታ ፍልሚያዎች ይደረጋሉ።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia

Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv