አዲስ አበባ | የካቲት 29፣ 2016| NBC ETHIOPIA -በየዓመቱ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በተመለከተ ከመገናኛ ብዙሃን ወይም በዙሪያዎ ካሉ ሰዎች ሰምተው ይሆናል ዕለቱ ለምን እንደሚከበር ብዙ ሰው አያውቅም ፤ ነገር ግን ይህ ዕለት ክብረ በዓል ወይስ የአመፅ ቀን?
የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ታሪካዊ መነሻውን ያደረገው የሠራተኞች እንቅስቃሴን ሲሆን በአሁኑ ወቅት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዕውቅና የተሰጠው ዓመታዊ በዓል ለመሆን በቅቷል፡፡
እንደ እ.ኤ.አ በ1908 በኒውዮርክ ከተማ 15 ሺህ የሚሆኑ ሴት የጋርመንት ሰራተኞች በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ከባድ የስራ ጫና ተከትሎ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል። በወቅቱ የሥራ ሰዓት መሻሻልን፣ የተሻለ ክፍያንና ሴቶች በምርጫ መሳተፍ አለባቸው የሚሉትና መሰል ሀሳቦችን በማንገብ ነበር የተቃውሞ ሰልፍ ያከሄዱት።
ከአንድ ዓመት በኋላም የአሜሪካ ሶሻሊስት ፓርቲ የመጀመሪያ ብሔራዊ የሴቶች ቀን አወጀ።ቀኑን ዓለም አቀፍ የማድረግ ሃሳቡ የመጣው ክላራ ዜትኪን በምትባል ግለሰብ አማካኝነት ነው።
በዴንማርኳ ኮፐንሃገን በእ.ኤ.አ 1910 የሴት ሠራተኞች ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ነበር ሃሳቡን ያነሳችው።በወቅቱ ከ17 አገራት የተውጣጡ 100 ሴቶች ተሳትፈውበት የነበረ ሲሆን በሃሳቡን ሙሉ በሙሉ ነው የተስማሙት።
ለመጀመሪያ ጊዜም በኦስትሪያ፣ ዴንማርክ፣ ጀርመንና ስዊዘርላንድ በእ.ኤ.አ 1911 መከበር ተጀመረ፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ መከበር የጀመረው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ክብረ በዓሉን ማክበር በጀመረባት በእ.ኤ.አ 1975 ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












