አዲስ አበባ | የካቲት 29፣ 2016| NBC ETHIOPIA -በዓለም አቀፍ ለ113ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሴቶች ቀን (ማርች 8) በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ 48ኛ ጊዜ ሴቶችን እናብቃ፤ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል በአድዋ ድል መታሰቢያ እየተከበረ ይገኛል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሴቶች ቀን ውብ በሆነው አድዋ ድል መታሰቢያ መካሄዱ ትልቅ ትርጉም አለው ብለዋል።
የሴቶች ቀን እንዲከበር ጠንካራ ትግል ተደርጓል እኔም ፕሬዚዳንት ለመሆን መሰረት ጥሎልኛል ብለዋል ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ።
ብዙ የኃላፊነት ቦታ ላይ የተቀመጥነውም ሴቶች አቅማችንን አስመስክረን ነው ብለዋል። የሴቶችን ተሳትፎ ጠንካራ ለማድረግ ትምህርት ላይ መሰራት አለበት ብለዋል።
በሀገር አቀፍ እየተከበረ በሚገኘው የሴቶች ቀን ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በመድረኩም የሴቶች ቀን ከማክበር ባሻገር የሴቶችን የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካና ማህበራዊ ተሳትፎ ለማጠናከር በርካታ ስራዎች መከናወናቸው ተነስቷል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ የሚያሳድጉ ስራዎች ማከናወኑን ገልጿል።የኢትዮጵያ ሴቶች አመራርነት ከየት ወደ የት? በሚል ርዕሰ ጉዳይ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












