አዲስ አበባ | ታህሳስ 26፤ 2016| NBC ETHIOPIA -አርሰናል የፊታችን እሁድ ሊቨርፑልን በሜዳው በሚያስተናግድበት የሶስተኛ ዙር የኤፍ ኤ ዋንጫ ጨዋታ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ ነጭ ማልያ ይለብሳል።

ይህ ተግባር ለንደን ውስጥ በወጣቶች የሚፈጸሙ የስለት ጥቃቶችን ለማስቆም በ2022 ጥር ወር ላይ ከአዲዳስ ጋር በመተባበር ያስጀመረው “ከአሁን በኋላ ቀይ የለም” (No More Red) ዘመቻ አካል መሆኑ ተነግሯል።
ማልያው ለሽያጭ አይቀርብም በማህበረሰቡ ውስጥ አውንታዊ ለውጥ ማምጣት ለቻሉ ግለሰቦች በሽልማት ይሰጣል እንጅ።
ይሁንና አርሰናል ከአዲዳስ ጋር በመተባበር ያመረታቸውን “No More Red” T- ሸርቶች በ30 ፓውንድ እንደሚሸጥና ገቢውን በፈረንጆች 2008 ሰሜን ለንደን ኢስሊንግተን አካባቢ በጩቤ ተወግቶ ለሞተው ታዳጊ ቤን ኪንሰላ ፋውንዴሽን እንደሚለግስ አስታውቆ ነበር።
በመዲናዋ ለንደን አሁንም ድረስ በጩቤ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እየተበራከቱ ስለመምጣታቸው ዘገባዎች ይጠቁማሉ።
ከሰሞኑ በፈረንጆች የገና ዋዜማ ሃሪ ፒትማን የተባለ የ16 ዓመት ታዳጊ በጩቤ ተወግቶ ህይወቱ ማለፉን መረጃው አስታውሷል።
የአርሰናል አማካይ ዴክላን ራይስ ይህ አሰቃቂ ተግባር ይቆም ዘንድ ሌሎችም እግር ኳስ ተጨዋቾች ዘመቻውን ተቀላቅለው አርዓያነት ያለው ተግባር እንዲፈጽሙ ጥሪ አቅርቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












